በአላህ ነቢይ ላይ ሶላዋት ማውረድ እና ትሩፋቱ

0
545

በአላህ ነቢይ ላይ ሶላዋት ማውረድ እና ትሩፋቱ

አላህ (ሱ.ወ.) በመልዕክተኛው ላይ ሶለዋት እንድናወርድ አዞናል፡፡

{إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا} سورة الأحزاب (56)

‹አላህ እና መላእክቱ በነቢዩ ላይ እዝነት ያወርዳሉ፡፡ እናንተም ያመናችሁ ሆይ! በርሱ ላይ እዝነትን አውርዱ፡፡ ሰላምታንም ሰላም በሉ፡፡› (አል-አሕዛብ ፡ 56) በማለት፡፡

የአላህ መልዕክተኛም (ሰ.ዐ.ወ.) ሥማቸው የተወሳ እንደሆነ በርሣቸው ላይ ሶለዋት እንድናወርድ አዘውናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በርሣቸው ላይ ሶለዋት ማውረድ ያለውን ምንዳም አውስተውልናል፡፡

عن أبي هريرة  رضي الله عنه قال: قال النبي صلى الله عليه وسلمفإنه من صلى علي واحدة صلى الله عليه بها عشرا. )أخرجه مسلم وأبو داود والترمذي

ከአቢ ሁረይራ (ረ.ዐ.) እንደተላለፈው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ‹በኔ ላይ አንዲት ሰላት ያወረደ ሰው አላህ በሷ ምክኒያት አሥር ሰላቶችን በሱ ላይ ያወርድበታል፡፡›

ሶለዋት ማለት የአላህ እዝነት ማለት ነው፡፡ በነቢዩ ላይ ሶለዋት ስናወርድ አላህ (ሱ.ወ.) በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) እዝነቱን እንዲያወርድ እየለመንን ነው ማለት ነው፡፡

በአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ላይ ሶለዋት ለማውረድ (ለርሣቸው የአላህን እዝነት ለመለመን) በርካታ አባባሎች የመጡ ቢሆንም ዑለማኦች ይበልጥ የመረጡትና የተሟላው አባባል ይህ ነው፡፡

(: اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد)

‹አልላሁምመ ሶልሊ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ሙሐመዲን ከማ ሶለይተ ዐላ ኢብራሂመ ወዐላ ኣሊ ኢብራሂም ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ፡፡ አልላሁምመ ባሪክ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ሙሐመዲን ከማ ባረክተ ዐላ ኢብራሂመ ወዐላ ኣሊ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ› የሚለው ነው፡፡

ትርጉሙ – ‹ አላህ ሆይ! በኢብራሂም እና በቤተሰቦቹ ላይ እዝነትህን እንዳወረድክ ሁሉ በሙሐመድ እና በቤተሰቦቹ ላይ እዝነትን አውርድ፡፡ አንተ ምስጉን እና የተከበርክ ነህና፡፡ አላህ ሆይ! በኢብራሂም እና በቤተሰቦቹ ላይ በረከትህን እንዳወረድክ ሁሉ በሙሐመድ እና በቤተሰቦቹም ላይ በረከትህን አውርድ፡፡ አንደ ምስጉን እና የተከበርክ ነህና፡፡›

በአላህ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሶለዋት ማውረድ ትልቅ ምንዳ አለው፡፡ በርሣቸው ላይ ሶለዋት አለማውረድ ንፉግነት ነው፡፡ ኪሳራ ያስከትላል፡፡ በተለይ ሰብሰብ ብለው በተነሱ ሰዎች ላይ፡፡ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል-

 

وعن أبي هريرة – رضي الله عنه – قال : قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم – : ” ما جلس قوم مجلسـًا لم يذكروا الله ولم يصلوا على نبيهم – صلى الله عليه وسلم – إلا كان مجلسهم عليهم ترة يوم القيامة ، إن شاء عفا عنهم وإن شاء أخذهم “(رواه الترمذي (

ከአቢ ሁረይራ (ረ.ዐ.) እንደተወራው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል ‹የአላህን ሣያወሱና በነቢያቸዉም ላይ ሰለዋት ሣያወርዱ በአንድ ስብስብ የተቀመጡ ሰዎች ስብስባቸው የኪሣራ ነው፡፡ ከሻ ይምራቸዋል፣ ከሻም ይቀጣቸዋል፡፡› (ቲርሚዚ ዘግበውታል)

በሌላ ሐዲሥም

عن علي بن أبي طالب رضي الله عنه:  البخيل من ذكرت عنده ثم لم يصل عليرواه أحمد 

ከዐሊ ኢብኑ አቢ ጣሊብ (ረ.ዐ.) እንደተወራው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.)‹ንፉግ ማለት ሥሜ በርሱ ዘንድ ተወስቶ በኔ ላይ ሰለዋት ያላወረደ ሰው ነው፡፡› ብለዋል፡፡

ሶለዋት ዐለ ነቢ ዛሬ ላይ እየተረሱ ካሉ ተግባራት መካከል አንዱ ነው፡፡ ታላቁ ዓሊም ኢብኑ አልቀይም (አላህ ይዘንላቸው) ነቢዩ ላይ ሶለዋት ማውረድ ስላለው ምንዳ አርባ ትሩፋቶችን ዘርዝረዋል፡፡ ከነኚህም መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ

 1. የአላህ ትዕዛዝ የማክበር ተምሳሌት ነው፡፡ አላህ አዞበታልና፡፡
 2. አንድ ሶለዋት አሥር እዝነት ከአላህ እናገኛለን፡፡
 3. አሥር ደረጃ ከፍ ያደርጋል፣
 4. አሥር ምንዳ ያስገኛል፣
 5. ፃድቃን ከሆኑ የአላህ መላእክት ጋር መገጣጠም ነው፤ እነርሱም ሶለዋት ያወርዳሉና
 6. አሥር ወንጀል ያሳብሳል፣
 7. የአንድ ሰው ዱዓእ ምላሽ ያገኝ ዘንድ አንዱ ምክንያት ነው፣
 8. በቂያማ ቀን የነቢዩን ምልጃ ያስገኛል፣
 9. የመልዕክተኛውን (ሰ.ዐ.ወ.) ሐቅ የምንወጣበት አንዱ መንገድ ነው፣
 • አላህ ካሳሰበን ነገር ሁሉ ይጠብቀናል፣
 • ሶላዋት የሚያበዛ የትንሳኤ ቀን የነቢዩን ጉርብትና ያገኛል፣
 • አላህ እና መላእክትም እዝነታቸውን ያወርዱልናል፣
 1. ነፍሳችንን ያጠራልናል፣
 • የረሳነውን ነገር ያስታውሰናል፣
 • ለአንድ ስብስብ ማስዋቢያና ምንዳ ማግኛ ነው፣
 • አላህን የማስታወስ እና የማመስገን አካል ነው፣
 • የነቢዩ ዉዴታ መገለጫ ነው፣
 • የአላህ እዝነት ለማግኘት ሰበብ ነው፣
 1. በረከትን ያስገኛል፣
 • ለመስተካከልና ለመፅናት ያግዛል

.www.alifradio.com