ዕውቀት የመገብየትና ቁርኣን የማንበብ ትሩፋት

0
684

ዕውቀት የመገብየትና ቁርኣን የማንበብ ትሩፋት

عَنْ عُقْبَةَ بْنِ عَامِرٍ، قَالَ:

خَرَجَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَنَحْنُ فِي الصُّفَّةِ، فَقَالَ:

((أَيُّكُمْ يُحِبُّ أَنْ يَغْدُوَ كُلَّ يَوْمٍ إِلَى بُطْحَانَ أَوْ إِلَى الْعَقِيقِ، فَيَأْتِيَ كُل يوم  بِنَاقَتَيْنِ كَوْمَاوَيْنِ زهراوين فيأخذهما فِي غَيْرِ إِثْمٍ، وَلَا قَطْعِ رَحِمٍ؟))

 

فَقُلْنَا: كلنا يَا رَسُولَ اللهِ! يحِبُّ ذَلِكَ!

قَالَ:

((أَفَلَا يَغْدُو أَحَدُكُمْ إِلَى الْمَسْجِدِ فَيَتعلَم، أَوْ يَقْرَأُ آيَتَيْنِ مِنْ كِتَابِ اللهِ عَزَّ وَجَلَّ؛ خَيْرٌ لَهُ مِنْ نَاقَتَيْنِ!

وَثَلَاثٌ؛ خَيْرٌ لَهُ مِنْ ثَلَاثٍ!

وَأَرْبَعٌ؛ خَيْرٌ لَهُ مِنْ أَرْبَعٍ!

وَمِنْ أَعْدَادِهِنَّ مِنَ الْإِبِلِ))!!

 

 

ዑቅባህ ኢብን ዓሚር (ረ.ዐ.) ባስተላለፉት ሐዲሥ እንዲህ አሉ ‹የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሰለም እኛ ወዳለንበት በረንዳ በመምጣት ‹በየዕለቱ ማለዳ ወደ ቡጥሐን ወይንም ወደ ዐቂቅ በመሔድ አንድም ወንጀል ሣይፈፅምና ዝምድናንም ሣይቆርጥ ሁለት ወፋፍራም ትላልቅ ሻኛ ያላቸው ግመሎችን ይዞ መምጣት የሚሻ ማነው?› አሉ፡፡ ሁላችንም ‹እንሻለን የአላህ መልእክተኛ ሆይ!›  አልናቸው፡፡  እርሳቸውም ‹እንግዲያውስ  ወደ መስጊድ ሒዱና ዕውቀት ገብዩ፤ ወይንም ከቁርኣን ሁለት አንቀፅ አንብቡ፡፡ ይህ ከሁለት ሴት ግመል ይሻላችኋል፡፡ ሦስት አንቀፅ ማንበብም ከሦስት ግመሎች የበለጠ ነው፡፡ አራት ማንበብም ከአራት ግመሎች የተሻለ ነው፡፡ ብዙ አንቀፆች መማር/ማንበብ ከብዙ ግመሎችም የተሻሉ ናቸው፡፡› በማለት ነገሩን። (ሙስሊም ዘግበውታል፡፡)

 

መጠነኛ ማብራሪያ

ቡጥሐንም ሆነ ዐቂቅ መዲና አቅራቢያ የሚገኝ የቦታ ሥም ነው፡፡ ግመል ደግሞ ዐረቦች ዘንድ እጅግ ዉድ እና ተፈላጊ እንሰሳ ነው፡፡ ሆኖም ግን ዕውቀት መገብየት እና ቁርኣንን የማንበብ ምንዳው ከየትኛውም ዓለማዊ ጥቅም የላቀ መሆኑን ለማሳየትና ሶሐቦቻቸውም ሆነ አማኞች ሁሉ ፊታቸውን ወደዚሁ በጎ ሥራ ያዞሩ ዘንድ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ይህንን ምሳሌ ለሰዎች በሚገባቸው መልኩ ተጠቅመዋል፡፡  ስለሆነም ይህንን ታላቅ ምንዳ እናገኝ ዘንድ በዕውቀት ፍለጋና የአላህን ቁርኣን በማንበብ መበርታት ይኖርብናል፡፡ የአላህን ቁርኣን መማር ትልቅ ክብር ነው፡፡ ምርጡ ሰውም ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረው ነው፡፡ አላህ ይወፍቀን፡፡

www.alifradio.com