ልዩ ልዩ መረጃዎች..

ካለፉት 3 አመታት ትርፉ ከፍተኛው ነው ተብሏል

ያለፉትን ወራት በእሳት ፈጣሪው ምርቱ በጋላክሲ ኖት 7 ሳቢያ ቀውስ ውስጥ ተዘፍቆ የገፋው ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩባንያ ሳምሰንግ፤ ባለፉት ሶስት አመታት ታሪኩ ከፍተኛው የተባለውን የ8.8 ቢሊዮን ዶላር የሩብ አመት ትርፍ ማስመዝገቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የደቡብ ኮርያው ሳምሰንግ እስካለፈው መጋቢት ወር ባለው ያለፈው ሩብ አመት ከፍተኛ የተባለውን ትርፍ ሊያስመዘግብ የቻለው፣ የሚሞሪ ቺፕስ፣ የቴሌቪዥን ፍላት ስክሪን እና የሞባይል ስልክ ምርቶቹ በተጠቃሚዎች ዘንድ ያላቸው ተፈላጊነት በመጨመሩ ነው ተብሏል፡፡
ኩባንያው በቀጣይም ትርፋማነቱን ከፍ አድርጎ እንደሚዘልቅ ይጠበቃል ያለው ዘገባው፣ ለዚህም በምክንያትነት የተጠቀሰው ከሰሞኑ ለገበያ ያቀረባቸው የጋላክሲ ኤስ 8 እና ኤስ 8 ፕላስ የሞባይል ምርቶቹ በገበያው ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኙ መምጣታቸው ነው መባሉን ገልጧል፡፡
ሳምሰንግ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ለገበያ ያቀረበው የጋላክሲ ኖት 7 ምርቱ፣ ባትሪው ከፍተኛ ሙቀትና እሳት እየፈጠረ አደጋ ማስከተሉን ተከትሎ ህልውናውን ስጋት ላይ የሚጥል ፈተና ውስጥ ገብቶ እንደነበር ያስታወሰው ዘገባው፣ ለደምበኞቹ ሽጧቸው የነበሩ 2.5 ሚሊዮን ያህል ምርቶቹን መልሶ መረከቡ ከፍተኛ ኪሳራ እንዳስከተለበትም አስታውሷል፡፡

ምንጭ =አዲስ አድማስ

የስልኮት ባትሪ በፍጥነት እያለቀ አስቸግሮታል? እንግዲያውስ የሚከተሉትን አማራጮችን ስክሎት ላይ በማስተካከል የባትሪዎትን ህይወት ማርዘም ይችላሉ፡፡ 1 ለወራት ያልተቀሙባቸውን አፕሊኬሽኖች ወይም መተግበሪያዎች ማጥፋት ስልኮት ላይ ጭነዋቸው ነገር ግን ለወራት ምንም ጥቅም ላይ ሳያውሏች ግን ኢንተርኔት በሚጠቀሙበት ጊዜ ኖቲፊኬሽን እና የመሳሰሉትን የሚልኩ አፕሊኬሽኖች የባትሪዎትን ህይወት ሊያሳጥሩት ይችላሉ፡፡ ስለዚህም እነኚህን አፕሊኬሽኖች ከስልኮት ላይ ማጥፋት የባትሪዎትን ህይወት ከማራዘም ባለፈ ከአላስፈላጊ የኢንተርኔት ወጪ ሊያድኖት ይችላል፡፡ 2 ጠቃሚ ያለሆኑ አፕሊኬሽኖች Background data እንዳይጠቀሙ ማድረግ ኢንተርኔት በሚጠቀሙበት ጊዜ Background data የሚጠቀሙ አፕሊኬሽኖችን ሴቲንግ ውስጥ በመግባት Background data እንዳይጠቀሙ በማድረግ የባትሪዎትን ህይወት ማራዘም ይችላሉ፡፡ ስለዚህም ብዙ ጊዜ የማይጠቀሙባቸውን አፕሊኬሽኖችን ወይም መተግበሪያዎች በመምረጥ Background data እንዳይጠቀሙ ማድረግ ይችላሉ፡፡ 3 በተደጋጋሚ አፕሊኬሽኖችን ከመዝጋትና መክፈት መቆጠብ ብዙ ጊዜ እንደነ ኦፔራ ሚኒ፣ፌስ ቢክ የመሳሰሉ አፕሊኬሽኖችን ተጠቅመን ስንጨርስ ዘግተን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መልሰን እንከፍታለን፡፡ ይህን ተግባር በተደጋጋሚ ባደረግን ቁጥር ለሞባይላችን ባትሪ ጠንቅ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ስለዚህም ከተጠቀምን በኋላ የሆም በተኑን ተጠቅመን በመውጣት ሌላ ጊዜ መጠቀም ስንፈልግ ሞባይላችን ካቆመበት እንዲቀጥል ያደርገዋል፡፡ ይህ ደግሞ የሞባይላችንን ባትሪ እድሜ እንዲኖረው ያደርገዋል፡፡ 4 የስልኮትን ቫይብሬሽን ማጥፋት ስልክን በሪንግቶን ብቻ መጠቀም ለብዙዎቻችን አስቸጋሪ እንደሚሆን ግልፅ ነው ሆኖም ግን የባትሪዎትን ህይወት ማስረዘም ሀሳብ ካለዎት ግን የስልኮን ቫይብሬሽን ማጥፋት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንንም ለማድረግ የስልኮት የድምፅ አማራጭ ላይ በመግባት የቫይብሬሽን አማራጭ ማጥፋት፡፡ 5 የስልኮን ብሉቱዝ አማራጭ ማጥፋቶን ማረጋገጥ አብዛኛዎቻችን ምንፈልገውን ነገር ከወዳጆቻችን ጋር ብሉቱዝን በመጠቀም ከተላላክን በኋላ ብሉቱዛችንን ማጥፋት እንዘነጋለን ይህ ደግሞ ለባትሪያችን ህይወት ማጠር እንደ ምክንያት ይነሳል፡፡ ለዚህም እንደአማራጭነት የቀረበው ሁልጊዜ ብሉቱዛችን መጥፋቱን ማረጋገጥ እንዲሁም ከሰዎች ጋር ዳታን ከተላላክን በኋላ ወዲያውኑ ማጥፋትን አለመዘንጋት ነው፡፡ ምንጭ፡ ታይም መፅሄት

www.alifradio.com

0 2341

ራሰ በራነት ምንድን ነው? መነሻው እና ህክምናው ምንድን ነው? (በዳንኤል አማረ) “ፀጉር በማንኛውም የሰውነታችን ቆዳ ላይ ከእጃችን መዳፍ እና ከእግራችን ሶል ዉጪ ይበቅላል ነገር ግን አብዛኛዎቹ ፀጉሮች ስስ ስለሆኑ በአይናችን ላናያቸው እንችላለን፡፡ ፀጉር ኬራቲን (keratin) ከሚባለው ፕሮቲን በዉጨኛው የቆዳ ክፍል የፀጉር ፎሊክል ዉስጥ ይሰራል፡፡ ፎሊክላችን አዲስ የፀጉር ሴል ሲሰራ/ሲያመርት አሮጌ ሴሎቻችን በአመት 6 ኢንች ወደ ዉጪ ቆዳችን ተገፍተው ይወጣሉ የምናየው ፀጉር የሞተ ክር መሳይ ኬራቲን ሴል ነው፡፡ በአማካይ የአንድ አዋቂ ሰው ጭንቅላት ከ 100,000-150,000 የሚደርስ ፀጉር ሲይዝ በቀን 100 ፍሬ ፀጉር በራሳቸው ጊዜ ይነቀላሉ በማበጠሪያች ውስጥ ትንሽ የተነቀሉ ፀጉር ማግኝት የተለመደ እና ሊያስደነግጠን የማይገባ ጤናማ ሁኔታ ነው፡፡

www.alifradio.com

0 1055

የአንዲት ተማሪ ወላጅ ልጃቸውን ሊያስመዘግቡ ቃሊቲ አካባቢ ወደሚገኘው ኖላዊ አፀደ ህፃናትና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ይሄዳሉ፡፡ ከትምህርት ቤቱ ባለቤት አቶ ተስፋዬ አግዘው ጋርም ይገናኛሉ፡፡ ወላጅ በውስጣቸው የጨነቃቸውን ነገር ለትምህርት ቤቱ ባለቤት ይተነፍሳሉ፡- “እኔ በህይወት ብዙ መቆየት አልችልም፤ እባካችሁ ልጄን እንደ ልጃችሁ ተንከባክባችሁ አሳድጉልኝ” በማለትም ይማፀናሉ፡፡
የትምህርት ቤቱ ባለቤት በሁኔታው በመደናገጥ “ምን ሆነው ነው?” ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ ወላጅ ከእንባቸው ጋር እየታገሉ፤ “የኩላሊት በሽተኛ ነኝ፤ መዳን አልችልም” አሉ፤በተስፋ መቁረጥ ስሜት፡፡
የትምህርት ቤቱ ባለቤትም፤ “እንግዲያውስ ግዴለም እንዳሉት አደርጋለሁ” ሲሉ ቃል ገብተው ይሸኟቸዋል፡፡ እኚህ ወላጅ ዛሬም የአልጋ ቁራኛ ሆነው ከህመማቸው ጋር እየታገሉ ይገኛሉ፡፡
አቶ ተስፋዬ ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ የሰውየው ነገር እረፍት እንደነሳቸው ይናገራሉ፡፡ ሁለት ቀን እንቅልፍ አልተኛሁም ነበር የሚሉት የት/ቤቱ ባለቤት፤ወዲያው በኩላሊት በሽታ ለሚሰቃዩ ወገኖች ለምን የአቅሜን አላደርግም በማለት ከተማሪዎችና ከአካባቢው ማህበረሰብ መዋጮ ለማሰባሰብ መወሰናቸውን ይናገራሉ፡፡ የትምህርት ቤታቸው የዓመቱ መዝጊያ በዓል በተከበረበት ባለፈው እሁድ ከተማሪዎች 7 ሺህ ብር የተሰበሰበ ሲሆን ከኪሳቸው 20 ሺህ ብር በመጨመር ፣በአጠቃላይ 27 ሺ ብር በስፍራው ተገኝተው ለነበሩት የኩላሊት ህሙማን ማህበር መስራቾችና ሊቀመንበር አስረክበዋል፡፡
በትምህርት ቤቱ የመዝጊያ ስነ ስርአት ላይ የታደሙት የተማሪ ቤተሰቦች በበኩላቸው 21 ሺህ ብር አዋጥተው ለኩላሊት ህሙማን ለግሰዋል፡፡
የትምህርት ቤቱ ባለቤት በቀጣይም ለኩላሊት ህሙማን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል የገቡ ሲሆን መሰል ተቋማትም ለህሙማኑ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
ገንዘቡን የተረከቡት የኩላሊት ህሙማን ማህበር አመራሮችም፣ገንዘቡ በቀጥታ ለህሙማኑ መታከሚያ እንደሚውል አስታውቀዋል፡፡
በአሁን ወቅት በወር በአማካይ 23 ሰዎች ኩላሊታቸው ተጎድቶ ወደ ዳያሊስስ ህክምና እንደሚመጡ የገለፁት የማህበሩ አመራሮች፤ ከታማሚዎቹ ከ60 በመቶ በላይ ያህሉ ዕድሜያቸው ከ16-30 የሚሆናቸው ወጣቶች ናቸው ብለዋል፡፡
“ህመሙ በአስጊ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው” ያሉት የማህበሩ ሊቀ መንበር አቶ ሰለሞን አሰፋ፤ በሁለት ወር ውስጥ በዘውዲቱ ሆስፒታል የተገነባው አዲሱ የህክምና ማዕከል ስራ እንደሚጀምር ጠቁመው፣ማዕከሉ አገልግሎቱን ሲጀምር አንድ ታማሚ ቀደም ሲል ለዳያሊስስ ህክምና በሳምንት የሚያወጣው እስከ 4 ሺህ ብር የሚደርስ ወጪ፣ ወደ 300 ብር ዝቅ ይላል ብለዋል፡፡ ለህሙማን ትልቅ ተስፋ ነው!!

source- addis admass

0 413

‹‹በአደጋ ወቅት ሰዎችን የሚጎዳው አለአግባብ አፋፍሶ ማንሳት ነው››

ጠብታ አምቡላንስ በሞተር ሳይክል የአምቡላንስ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን አገልግሎቱ በአምቡላንስ መዘግየት ሳቢያ ህይወታቸውን የሚያጡ ወገኖችን ይታደጋል ተብሏል፡፡
የጠብታ አምቡላንስ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ክብረት አበበ ሰሞኑን ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የሞተርሳይክል የአንቡላንስ አገልግሎት በመንገዶች መዘጋጋትና በትራፊክ መጨናነቅ ሳቢያ አንቡላንሶች በወቅቱ ከሚፈለጉበት ሥፍራ ደርሰው አፋጣኝ እርዳታ ለመስጠት ባለመቻላቸው ምክንያት ለከፋ ጉዳትና ለሞት የሚዳረጉ ወገኖችን በእጅጉ የሚታደግና በተለይ ከመኪና አደጋ ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ ጉዳቶች ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡ የሞተር ሳይክል አምቡላንሶቹ ህሙማኑን የማጓጓዝ ሥራ እንደማይሰሩ የገለፁት አቶ ክብረት፤ በአግባቡ የሰለጠኑ የህክምና ባለሙያዎች የህይወት አድን መሳሪያዎችን ታጥቀው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሥፍራው በመድረስ ለህመምተኛው የህክምና እርዳታ እየሰጡ አምቡላንሱ እስከሚደርስ ድረስ የሚጠብቁ ናቸው ብለዋል፡፡ ይህም፤ በደም መፍሰስ፣ በትንፋሽ እጥረትና በልብ መቆም ችግሮች ሕይወታቸው የሚያልፍ ወገኖችን ለመታደግ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡በአደጋ ወቅት የሞተር ሳይክል አንቡላንሶቹ የትራፊክ መጨናነቅ ቢኖርም እንኳን ተሸሎክልከው በመድረስ ጉዳተኞቹ የከፋ ችግር ሳያጋጥማቸው ከአደጋው ስፍራ እንዲነሱና ህይወት አድን ህክምና ለማግኘት እንዲችሉ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ እገዛ ይሰጣሉ ብለዋል፡፡ በአደጋ ወቅት ከአደጋው ይልቅ ሰዎችን የሚጎዳው አለአግባብ አፋፍሶ ማንሳት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ክብረት፤ በአደጋው ከሚሞቱት ሰዎች ይልቅ በአያያዝ ችግር ህይወታቸውን የሚያጡት ሰዎች በቁጥር ይልቃሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የሞተር ሳይክል አገልግሎቱን ለማስጀመር ዝግጅቱ መጠናቀቁንና የሞተር ሳይክል ግዥ፣ ባለሙያዎችን የማሰልጠኑ መሳሪያዎቹን የማሟላቱ ስራ በመጠናቀቁ በቅርቡ ስራ እንደሚጀመር አቶ ክብረት ገልፀዋል፡፡

source -adissadmassmotorcycle-clip-art-by-naturaldigital-redbubble-cI21PD-clipart

0 2028

mother-1

በትግራይ ክልል በሽሬ እንደስላሴ ቀበሌ 05 ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ኢልሃም ብርሃኑ በሽር በአንድ ጊዜ የአራት ልጆች እናት ሆነች::

የአራት ልጆች እናት የሆነችው ወ/ሮ ኢልሃም በሽር ከባለቤቷ ከማል አብዱልዋስ ጋር የጋብቻ ስነስርዓቷን የፈጸመችው ሰኔ 3 ቀን 2005ዓ.ም ነበር፡፡ ይህች ወጣት እናት በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን የተገላገለችው እዚያው ሽሬ እንደስላሴ ውስጥ በሚገኘው ሱኁል ሆስፒታል መሆኑንም ታውቋል::

ለዘ-ሐበሻ እንደደረሰው መረጃ እናት ወ/ሮ ኢልሃም አራት ልጆችን በአንድ ጊዜ ከተገላገለች በኋላ “በ እርግዝና ወቅት ምንም የተለየ የሚሰማኝ ስሜት አልነበረም; በጥሩ ሁኔታ በሰላም ተገላግያለሁ” ብላለች:: አራቱን ልጆች ያዋለዱት ዶ/ር እዮብ ገላን “ወ/ሮ ኢልሃምም ሆነ ልጆቿ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ” ብለዋል::
source=the habeshesa

0 539

 

 

 

 

  • ሰሞኑን 35 ስደተኞች የያዘ ጀልባ የመን ሳይደርስ ሰጥሟል
  • በዓመት 200 ገደማ ኢትዮጵያውያን በበረሃ እና በባህር ጉዞ ላይ ሞተዋል
  • “በህጋዊ ምዝገባ የስራ ጉዞ መታገዱ ህገወጥ ስደትን አባብሷል”

በህጋዊ ምዝገባ ወደ አረብ አገራት የሚደረግ ጉዞ ከታገደ ወዲህ፣ በየመን በኩል እየተሰደዱ ለአደጋ የሚጋለጡ ኢትዮጵያዊያን መበራከታቸውንና ባለፉት ስድስት ወራት 47ሺ ያህል ስደተኞች የመን እንደገቡ RMMS ሰሞኑን ገለፁ፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን እና ሌሎች አለማቀፍ ድርጅቶች በጋራ ያቋቋሙት ይሄው ተቋም እንደሚለው፣ ዘንድሮ የስደተኞቹ ቁጥር ከአምናው በእጥፍ ይበልጣል፡፡ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት ውስጥ 250 ስደተኞች የመን ለመግባት ሲሞክሩ፣ በባህርና በበረሃ ጉዞ ላይ መሞታቸውን ተቋሙ ጠቅሶ ከስደተኞቹ መካከል ሰማኒያ በመቶ ያህሉ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ሰሞኑን በባህር ጉዞ ላይ በተፈጠረ አደጋ አንድ ጀልባ መስመጡን የዘገበው ኤኤፍፒ፤ ጀልባዋ 35 ስደተኞችን አሳፍራ ነበር ብሏል፡፡ ከጉዞ አደጋ በተጨማሪ ስደተኞቹ የመን ከገቡ በኋላም ግማሽ ያህሉ በወሮበላ ቡድኖች እንደሚታገዱ የገለፀው RMMS፤ ከእገታ ለመለቀቅ ከቤተሰብ ገንዘብ እንዲያስልኩ ይገደዳሉ ብሏል፡፡ ለስደት የሚገፋፉ ዋና ዋና ምክንያቶችን ለማወቅ በሺ በሚቆጠሩ ስደተኞችና በትውልድ አካባቢዎቻቸው ላይ ጥናት ያካሄደው ይሄው ተቋም፤ በኢትዮጵያ ዋናዎቹ መንስኤዎች የኑሮ ችግር እንዲሁም ህይወትን የሚያሻሽል ነገር ፍለጋ ናቸው ብሏል፡፡ የፖለቲካ ችግርም የተወሰነ ጫና እንደሚፈጥር ተቋሙ ጠቅሶ፣ የደላሎች ድርሻ ግን ብዙዎች እንደሚያስቡት አይደለም፤ ከመቶ ስደተኞች መካከል በደላላ ግፊት ለስደት የሚነሳሱት ከሁለት ወይም ከሦስት አይበልጡም ብሏል፡፡
ብዙ ወጣቶች ወደ ስደት የሚያቀኑት አደጋ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ባለማወቃቸው ነው ለማለት እንደሚያስቸግር ተቋሙ ሲያስረዳ፤ በአመት ውስጥ ወደ የመን ከገቡት ኢትዮጵያዊያን መካከል ሩብ ያህሉ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የተባረሩና ካሁን በፊት ስደትን የሞከሩ ናቸው ብሏል፡፡ ከቅርብ ወራት ወዲህ የስደተኞቹ ቁጥር የተባባሰበት ሌላው ምክንያት፣ በህጋዊ ምዝገባ ወደ ሳዑዲ አረቢያና ወደ ኩዌት ሲደረግ የነበረው የስራ ጉዞ በመንግስት መታገዱ ነው ብሏል – የተቋሙ ጥናት፡፡ በሌላ በኩል ሶማሊያ ውስጥ ከድህነት በተጨማሪ የሰላም እጦት ወጣቶችን ለስደት እንደሚገፋፋ ተቋሙ ገልፆ፤ በኤርትራ ደግሞ ከኑሮ ችግር ሌላ ዋነኛው ግፊት የመንግስት ከፍተኛ የፖለቲካ አፈና ነው ብሏል፡፡ በሊቢያና በግብጽ በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት ከሚሞክሩ ስደተኞች መካከል ከሶሪያዊያን በመቀጠል በቀዳሚነት የሚጠቀሱት ኤርትራዊያን መሆናቸውን የጠቀሰው ይሄው ተቋም፤ ባለፉት አራት ወራት 15ሺ ኤርትራዊያን ወደ ኢትዮጵያ እንደተሰደዱ ገልጿል፡፡ ስደት የተባባሰው በድህነትና በአፈና ምክንያት አይደለም በማለት የኤርትራ መንግስት ሲያስተባብል፤ ወጣቶች እንዲሰደዱ በማድረግ አገሪቱን ኦና ለማድረግ አለማቀፍ ሴራ እየተካሄደብኝ ነው ብሏል፡፡

source=addisadmass

CAIRO: Young German footballer Danny Blum has announced his reversion to Islam, describing it as a religion of hope and strength.

Danny Blum said, “Islam gave me strength. Pray calms my soul.”

“I was short-tempered, erratic and did not know where I belong,” he added.

misconception

Blum joined FC Nürnberg in Bavaria last July. The team plays in the he Second Division of professional football in Germany, the Bundesliga.

Shortly after joining the team, he injured his knee and was forced eventually to take six months off.

A few weeks ago, he took the decision to revert to Islam, joining the world’s fastest growing religion. “Living in the lap of luxury. Every weekend make alarm. No responsibility for anything. And what actually comes after retirement?” the questions came to Blum as he sat at home.

“I have visited a mosque and I immediately risen the heart. I felt this is something for me and wanted to know more,” Blum told Bild.

Ever since, he prays five times a day and eat halal food. Informing his parents with his decision, the 24-year-old player said they were scare at first.

“They are devout Christians. But soon they said that I have to go that route if I believe that it is right,” he said.

0 760

እንሆ የኮኪት ታላቁ ሀምዛ መስጂድ በደማቅ ሁኔታ ተመርቀ..  ጥር 17 2007 ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ከአ/አ 900 ኪሜ አካባቢ በምትርቀው ሞቃታማዋ ከተማ ኮኪት በአላህ ፈቃድ  የሀገሬው ነዋሪ ቀድሞን የመስጂዱን ቅጥር ግቢ ሞልቶት ነበር።መስጅድ ሊመረቅ ነው የተባለው የአካባቢው ተወላጅ በደስታ ጉድ ይላል የሚገርመው ነገር መስጅዱን ለማስመረቅ የተገኘው ሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን ክርስቲያኑም ጭምር መሆኑ ነው።
ግቢው በተለያየ ሀገር  ዲኮር ደምቋል የሁሉም ሰው ፊት በፈገግታ እና እርካታ ደምቋል ::

     ይህ መስጅዱ ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ ወደ 5 ሚሊዩን ብር ፈጅቷል::
ሙሰሊም ከኸይር ስራ አይሰለችም 

 

 

የፍቅር ቦንብ (በሙሳ ኑረዲን)
በሲውዲን uppsala ከተማ ለሁለት ጊዜ በመስጊድ ላይ ጥቃት ከተደረገ ሳምንት ሳይሞላው በሌላ ሶስተኛ ጥቃት አንድ መስጂድ መቃጠሉን ከዜና አውታሮች ሰማሁ:: በመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ጥቃቶች መስጂድ ውስጥ በነበሩ ሙስሉሞች ላይ ጉዳት ደርሷል::
መስጂዱ በእሳት እንዲያያዝ ምክንያት በሆነው በሶስተኛው ጥቃት ግን በመስጂዱ ውስጥ ማንም ሰው እናዳልነበር ለማወቅ ተችሏል:: አልሀምዱሊላህ
ይህንን አደጋ ያደረሱት ስዎች ወደ መስጂዱ በጋዝ የተሞላ የጠርሙስ ቦንብ ሲወረውሩ እና የጥላቻ ንግግሮችን በመስጂዱ ግድግዳ ላይ ሲፅፉ እንዳዩ የአይን እማኞች ገልፀዋል::
እኔን ያስገረመኝ ግን ይህ አይደለም!!!
የሲውዲን ጠቅላይ ሚንስትር ስለድርጊቱ እንዲህ ብለዋል ፦ ” ይህ ሲውዲን አይደለም:: የሲውዲኖች መንገድም አይደለም:: ሲውዲናዊ እንዲህ አያደርግም::”
በአደጋው ማግስት ይህንን ኢ ስብአዊ ድርጊት የማይደግፉና ሙስሊም ያልሆኑ የኣካባቢው ነዋሪዎች እደግመዋለሁ ሙስሊም ያልሆኑ የኣካባቢው ነዋሪዎች የመስጁዱን በር ቀያይ ቀለም ባላቸው በልብ ቅርፅ በተስሩ ወረቀቶች አጨናንቀውታል:: እምርረው እንደሚቃወሙትም የሲውዲኖች መንገድ እንዳልሆነም ገልፀዋል:: ለኔ ከዛ መሀይም የጠርሙስ ቦንብ ይልቅ የነዚህ ስዎች የፍቅር ቦንብ ገዝፎ ታይቶኛል:: ማንም ሁን ምንም ከእውነት ጋር መቆም ሊያስደስትህ ይገባል:: ቤተሰብ ዝምድና ወገንተኝነት እውነት ላይ ቦታ የላቸውም:: ነፍስያህ እንኳን ሀቅን ብትቃረን ነጠል ብለህ ቆመህ ተቃወማት:: ሲውዲኖች ጥሩ ሱና ነው ብያለሁ:: ይህ አርቆ አሳቢነት ደግሞ በኛ በሀበሾችም ዘንድ ቢኖር ወደድኩ::