ጤናችን

0 8369

ማንኮራፋት የምንለው በምንተኛበት ጊዜ በመተንፈሻ አካላችን ላይ በሚፈጠሩ ለውጦች ምክንያት በሚመጣ ድምፅ ነው። ማንኮራፋት አብሮ የሚተኛን ሰው ከመረበሽ ባለፈ አንዳንድ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የጤና እክሎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

► ለማንኮራፋት ተጋላጭነት የሚዳርጉ ሁኔታዎች

የሰውንት ክብደት መጨመር:- በተፈጥሮ የሚኖር ጠባብ መተንፈሻ አየር የምናስገባበት አካል መጥበብ የምንስበው አየር ግፊት እንዲጨምር በማድረግ ድምፅን ይፈጥራል

አልኮል መጠጥ ማብዛት፡- የአልኮል መጠጥ የጉሮሮ ጡንቻዎችን በማፍታታት አየር በሚገባበት ወቅት ርግብግቢት በመፍጠር ድምፅ እንዲጨመር ያደርጋል

በአፍንጫ ላይ የሚከሰቱ ችግሮች፡- በአፍንጫ ላይ የሚኖሩ ተፈጥሮአዊ የአቀማመጥ ችግሮች የማንኮራፋት ዕድልን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ

► ማናኮራፋት የሚያስከትላቸው ችግሮች

ቀን ቀን የእንቅልፍ ስሜት መሰማት
ብስጭትና ንዴት
ለነገሮች ትኩረት ማጣት
ለደም ግፊትና ለልብ ሕመም ማጋለጥ
በእንቅልፍ እጦት ምክንያት ለሰው ሠራሽ አደጋዎች መጋለጥ
የትዳር አጋርን እንቅልፍ ማሳጣት ናቸው፡፡

► የሚያንኮራፉ ሰዎች

✔ በእንቅልፍ ጊዜ የሚረብሽ ድምፅ ያሰማሉ
✔ የቀን እንቅልፍ ሊያስቸግራቸው ይችላል
✔ የጉሮሮ መከርከር ይኖርባቸዋል
✔ ሰላም የሌለው እንቅልፍ ያስቸግራቸዋል
✔ በእንቅለፍ ጊዜ ትንታ እና ትንፋሽ ማጠር ያጠቃቸዋል
✔ የደረት መጨምደድና የደም ግፊት ሊኖራቸው ይችላል፡፡

► ማንኮራፋትን የምንከላከልባቸው መንገዶች

✔ አስተኛኘትዎን ያስተካክሉ

በጀርባዎ መተኛት ምክንያት እና ለስላሳ ላንቃዎን ወደ ጉሮሮ እንዲወርዱ ስለሚያደርግ በእንቅልፍ ጊዜ የመርገብገብ ድምፅን እንዳናሰማ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ በጎን መተኛት መፍትሔ ሊሆን ይችላል፡፡

✔ የሰውነት ክብደትዎን ይቀንሱ

የሰውነት ክብደት የሌላቸው ሰዎችም ቢሆኑ ያንኮራፋሉ፡፡ ነገር ግን ማንኮራፋቱ የመጣው የሰውንት ክብደት ከጨመረ በኋላ ከሆነ መንስዔው ሊሆን ስለሚችል ክብደትዎን ይቀንሱ፡፡

✔ የአልኮል መጠጥ አይውሰዱ

የአልኮል መጠጥ የምንወስድ ከሆነ በጉሮሮ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎችን ስለምናፍታታ ማንኮራፋት እንጀምራለን፡፡ ከመተኛታችን በፊት ባለው ከ4 – 5 ሰዓት ጊዜ ውስጥ አልኮል መጠጥን መውሰድ ማናኮራፋትን ያባብሳል፡፡

✔ የእንቅልፍ ሰዓትዎን ያስተካክሉ

ለረጅም ሰዓታት ያለዕረፍት የሚሠሩ ከሆነ እና በመጨረሻ እጅግ በጣም እራስዎን ካዳከሙ በኋላ የሚተኙ ከሆነ የጉሮሮ ጡንቻዎች ባጣም ስለሚፈታቱ የማንኮራፋት ድምፅ ያሰማሉ፡፡

✔ አፍንጫዎን ከመደፈን ይከላከሉ

አፍንጫዎ በቅዝቃዜም ሆነ በአለርጂ ምክንያት ከተደፈነ የማንኮራፋት ዕድልን ሰለሚጨምር ከመተኛትዎ በፊት በሙቅ ውሃ ገላን መታጠብ በተጨማሪ ውሃ በጨው በማድረግ አፍንጫን ማፅዳት፡፡ ይህ የአፍንጫን ቀዳዳዎች ስለሚከፍት ማንኮራፋትን ይከላከላል፡፡

✔ ትራሰዎን የቀይሩ

በትራስዎ ውስጥ በዓይን የማይታዩ ብናኞች ተከማችተው ሊገኙ ስለሚችሉ መቀየር ተገቢ ነው፡፡

✔ ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ

ፈሳሽን በብዛት መውሰድ ከአፍንጫችን የሚመነጨውን ፈሳሽ ሰለሚያቀጥን ማነኮራፋት እንዳይኖር ይረዳል፡፡

#ከማህደረ ጤና

0 1128

ልጅ ወልደው መሳም የሚፈልጉ ሴቶች የሚያዘወትሯቸውን መጥፎ ተግባራት ማስወገድ እንዳለባቸው ባለሙያዎች ይመክራሉ። በእርግዝና ወቅትም ጎጂ ነገሮችን አለማድረግ ፅንሱ እናቱን እንዲያመሰግን የሚያስችል ሲሆን ለእናትም ጤናን ይሰጣል ነው የሚሉት ባለሙያዎቹ፤ ገንዘብንም ይቆጥባል ተብሏል፡፡ በመሆኑም ልጅ ወልዳ መሳም የምትፈልግ እናት ከሚከተሉት አምስት መጥፎ ልማዶች መራቅ ይገባታል፡፡ 1. ሲጋራ ማጨስ በእርግዝና ወቅት ከሚያጋጥም የተዛባ የደም ዝውውር፣ የአተነፋፈስ ችግር፣ የሳንባ ጉዳት በመጠበቅ ፅንሱ ተገቢውን ደም፣ ምግብ እና ኦክስጅን እንዲያገኝ ለማድረግ ሲጋራ ከማጨስ መቆጠብ ተገቢ ነው ተብሏል፡፡ ይህም መሆን ያለበት ከእርግዝና በፊት፣ በእርግዝና ወቅት እና ከወሊድ በኋላ ሲሆን፥ ካርቦን ሞኖ ኦክሳይድ እና ኒኮቲንን በውስጡ የያዘውን ሲጋራን በመራቅ ለእርግዝና መዘጋጀት ወሳኝ መሆኑ ተመክሯል፡፡ በእርግዝና ወቅትም እናት እና ልጅ ጤናማ እንዲሆኑ የሚረዳ ሲሆን፥ በድህረ ወሊድ ጊዜም በፅንስ ጊዜ የሚያጋጥሙ በሽታዎች በልጅ ላይ እንዳይከሰቱ፣ ክብደታቸውም ጥሩ እንዲሆን ያደርጋል ሲል የአሜሪካ የእርግዝና ማህበር ጠቁሟል፡፡ 2. አልኮልን ወይም አነቃቂ ዕፆችን መጠቀም በእርግጥ ኢስላም ሀራም ያደረገው ብዙ ምክንያቶችም እንዳሉና ትልቅ ወንጀልና የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል መሆኑን ሁላችንም እንረዳለን ፡፡ የአሜሪካው የእርግዝና ማህበር በበኩሉ አልኮል ከእናት የእንግዴ ልጅ አልፎ በልጅ ወይም በፅንሱ ላይ ጉዳት ያስከትላል ነው የሚለው፡፡ ይህም ማለት አበው ሲናገሩ “የሚታይ እንጂ የማይበላ ፍሬ” እንዲሉ የማይወለድን ፅንስ በአልኮል መጠጥ ማሳደግ እንደ ማለት ነው ይላል ማህበሩ፡፡ አልኮል መጠጣትን በቅድመ እርግዝና ወቅት ማቆም ካልተቻለ ጎጂ ልማዱ በእርግዝናም ወቅት ቀጥሎ፥ ሽሉ ላይ ተፅዕኖ በማሳደር ከመደበኛው ጊዜ ቀድሞ መወለድን፣ የፅንስ መጨናገፍን፣ የህጻኑን ክብደት መቀነስን እና የእድገት መቀጨጭን ሁሉ እንደሚያስከትል ነው ያነሳው ማህበሩ፡፡ 3. ተገቢ ያልሆነ አመጋገብ “ሰዎች የሚመገቡትን ይመስላሉ” የሚል የፈረንጆች አባባል አለ፤ ታዲያ በሆዷ ውስጥ ሰውን ያህል ፍጡር የተሸከመች እርጉዝ እናት ከእርግዝናዋ በፊትም ሆነ በእርግዝናዋ ወቅት አመጋገቧን መለየት አለባት፡፡ በተለይም ከእርግዝና በፊት የተገኘውን ሁሉ የመመገብ ልማድ ካላት፥ በእርግዝና ወቅት ጣጣ እንዳያስከትል ጥንቅቄ እና ውሳኔ ማድረግ ያስፈልጋታል፡፡ በመሆኑም አንዲት እርጉዝ እናት በእርግዝና ወቅትም ሆነ ከእርግዝና በኋላ ስላለው ተገቢ እና የተመጣጠነ አመጋገቧ ትኩረት ማድረግ ይኖርባታል፡፡ አትክልት እና ፍራፍሬን፣ ጥራጥሬ ምግቦችን፣ ፕሮቲኖችን እና ሌሎችም ገንቢ እና ኃይል ሰጪ ምግቦችን መውሰድ ለራሷም ሆነ በሆዷ ውስጥ ላለው ልጇ ጤና ፋይዳው ብዙ ነው፡፡ ከፍተኛ የሆነ የሶዲየም እና የስኳር መጠን ያላቸውን ምግቦች፣ በማምከኛ ውስጥ ያልገቡ የስጋ እና ወተት ተዋፅኦዎችን እና በአግባቡ ያልታጠቡ ምግቦችን እንድትጠቀም አይመከርም፡፡ 4. ከመጠን በታች ወይም ከመጠን ያለፈ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ለእለት ተዕለት ጤናችን መልካም ነው፡፡ ከፍተኛ የስብ መጠንን ለማስወገድ፣ የስኳር በሽታን ለመቀነስ፣ ኃይል እና ጥንካሬን ለመጨመር፣ የጀርባ ህመመን ለማስታገስ ሁሉ ይረዳል፡፡ ሆኖም በጣም አድካሚ በሌላ በኩልም በጣም ትንሽ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ጉዳት ያስከትላል፡፡ በተለይም ሴቶች ከመጠን በላይ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ከሆነ፥ እንቁላል እንዳያመርቱ፣ የወር አበባም እንዳያዩ በማድረግ የእርግዝና ህልማቸውን ሊያቀጭጭባቸው ይችላል፡፡ በጣም ትንሽ የአካል እንቅስቃሴ ደግሞ ለውፍረት እና ለስኳር በሽታ ሊያጋልጥ እንደሚችል፥ ይህ ደግሞ ሴቶች እንዳያረግዙ የሚያግድ ሌላ ጣጣ እንደሚያመጣባቸው ጠቁመዋል፡፡ ስለሆነም ልጅ ወልደው መሳም የሚፈልጉ ሴቶች በአቅማቸው ልክ፥ በተለይም እስከ 30 ደቂቃ የሚደርስ የተመጠነ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸው ነው ባለሙያዎች የሚመክሩት፡፡ 5. ድካም ሲኖር እረፍት አለማድረግ የትኛዋንም እናት ብትጠይቁ ልጅ ማሳደግ ከባድ ኃላፊነት ነው፤ በመሆኑም ለሆርሞን ምጣኔ እና ለማንኛውም ጤና እንደ እናት እረፍት ያስፈልጋታል ይላል የአሜሪካው ብሔራዊ የእንቅልፍ ፋውንዴሽን፡፡ በመሆኑም በየቀኑ በትንሹ ለ20 ደቂቃ የእንቅልፍ ሸለብታ መውሰድ ተገቢ ነው፡፡ በመሆኑም አንድ እርጉዝ ሴት ድካም ሲሰማት በደመነፍስ የእግር ጉዞ ከማድረግ ይልቅ ሸለብታን የግድ መጠቀም አለባት የሚል ምክር አለው ፋውንዴሽኑ፡፡ ምንጭ፡-http://health.howstuffworks.com/

www.alifradio.com

0 3271

የሆድ ድርቀት በርካታ ሰዎችን ሲያጋጥም ይስተዋላል። ለዚህ ህመም የሚጋለጡ ሰዎችን ወደ ወጸዳጃ ቤት ሄደው በሚጸዳዱበት ወቅት በጣም ሲቸገሩም ይስተዋላል። ችግሩን ለመከላከል ይረዳን ዘንድም በቀላሉ በምናገኛቸው ነገሮች እራሳችንን መርዳት እንችላለን። ሎሚ፦ ሎሚ በውስጡ ባለው የሲትሪክ አሲድ አማካኝነት የምግብ መፈጨት ስርዓታችን የተስተካከለ እንዲሆን ይረዳል። ስለዚህም ሎሚን አዘውትሮ መበጠቀም ከሆድ ድርቀት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ችግሮችን መከላከል ይቻለል። በፋይበር የበለጸጉ ምግቦች፦ በፋይበር የበለጸጉ መግቦች የሆድ ድርቀትን ለመከላከል እንደሚረዱም ተጠቁሟል። ስለዚህም እንደ አጃ፣ ሩዝ፣ ገብስ፣ በቆሎ እና ሌሎች በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን በእለት ተእለት ምግባችን ውስጥ አዘውትሮ መውሰድ ይመከራል። ካፌይን ፦ እንደ ቡና አይነት ያሉ የካፌይን ንጥረ ነገሮች ያላቸውን አዘውትሮ መውሰድም ከሆድ ደርቀት ለመገላገል ይመከራል። ዘይት፦ ዘይት ወይም ቅባትነት ያላቸው ምግቦችም እንደ ሰገራ ያሉ ነገሮች በቀላሉ እንዲዘዋወሩ በማድረግ የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ይረዳሉ። ስለዚህም ዘይትነት ያላቸውን ምግቦች እና ዘይት በምግባችን ውስጥ በዛ አድርገን በመጠቀም የሆድ ድረቀትን መከላከል እንችላለን። ምንጭ፦ healthdigezt.com

www.alifradio.com

0 502

ጊንጥ በዓለማችን በአብዛኛው ቦታዎች ይገኛል፡፡ በበረሃ፣ በጫካ እና ሞቃት ቦታዎች ላይ በብዛት ይገኛል፡፡ ጊንጦች በአብዛኛው ንቁ የሚሆኑት በለሊት ክፍለ ጊዜ ነው፡፡ በእርጥበታማ ቦታዎች ላይ ያሉ ጊንጦች ቀለማቸው ወደ ቡናማ እና ጥቁር ሲያደላ፣ በበረሃማ አካባቢዎች ያሉት ጊንጦች ደግሞ ቀለማቸው ቢጫ ወይም ፈዛዛ አረንጓዴ ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ ሰው በጊንጥ ተነድፎ ህይወቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ ጊንጦች መርዛቸውን የሚሸከሙት ከጭራቸው ጫፍ ላይ ነው፡፡ ጊንጦች በጭራቸው ላይ በሚገኙት ሁለት እጢዎች አማካኝነት መርዛማ ውህድ የሚያመነጩ ሲሆን ይህንን መርዛቸውን ወደሌሎች በመውጋት ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡ በመርዛቸው የተነደፈ ሰው ወይም እንስሳ፣ ሰውነቱ ቀስ እያለ በመዝለፍለፍና አቅም በማጣት መንቀሳቀስ የሚያቅተው ይሆናል፡፡ በጊንጦች ንድፊያ ህይወት ሊጠፋ የሚችልበት አጋጣሚው አለ፤ በተለይ ህፃናት ላይ፡፡
ሁሉም የጊንጥ ዝርያዎች መርዛማ ናቸው፤ ነገር ግን የጉዳት መጠናቸው ይለያያል፡፡ የሚያደርሱት ጉዳት ሁለት አይነት ነው፡፡ አንደኛው፣ በተነደፍንበት ቦታ ላይ ብቻ ከፍተኛ ህመምና እብጠት የሚፈጥር ሲሆን በተጨማሪም በአፋችንና በምላሳችን ላይ ያበጠ ወይም የወፈረ የሚመስል ስሜት ያለው ነው፡፡ ሁለተኛው፣ የተነደፍንበትን ቦታ ጨምሮ ሙሉ የሰውነታችንን ሥርዓት የሚያዛባ ነው፡፡ ለምሳሌ ለመተንፈስ መቸገር፣ ለማየት መቸገር ወይም ብዥታ፣ የሽንት ወይም የሰገራ ማምለጥ፣ የልብ ምት ማቆም፣ የለሃጭ መዝረብረብ፣ ከፍተኛ መወራጨት፣ የሆድ እና የጨጓራ ምቾት ማጣት ናቸው፡፡ ሁኔታው ባጠቃላይ የሞት ጣር የሚመስል ስሜት ይፈጥራል፡፡ አልፎ አልፎም ሞትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ አደጋው በህፃናት ላይ የከፋ ውጤት ይኖረዋል፡፡ ሕክምናው፣ ጉዳቱ የደረሰበት ሰው በፍጥነት ማርከሻውን/አንቲቬኒን (Antivenin) ካልተወጋ እስከሞት ሊያደርሰው ይችላል፡፡
====ለተነደፈ ሰው ፈጣን እርዳታ ማድረግ====
>> የተነደፈውን ሰው እንዳይንቀሳቀስ ማስተኛት፣
>> በጨርቅ ወይም በገመድ ከተነደፈው ቦታ በላይ አጥብቆ ማሰር፣
>> እብጠት ወዲያው ስለሚፈጠር ሰዓት፣ የጣት ቀለበት እና የእጅ አምባር የመሳሰሉትን ቁሶች በፍጥነት ማውለቅ፣
>> የተነደፈውን ቦታ ማፅዳት፣
>> ንፁህ አየር እንዲያገኝ መርዳት፤ ራሱን ከሳተም የአፍ-ለ-አፍ ትንፋሽ የመጀመሪያ እርዳታ ማድረግ፣
>> የተነደፈውን ቦታ በስለት በመብጣት እየጨመቁ ፈሳሹ እዲወጣ ማድረግ፣
>> የተነከሰው ሰው በተቻለ ፍጥነት የማርከሻ(Antivenin) መርፌ እንዲወጋ መደረግ አለበት፤ ይህን ማድረግ ካልቻልን የሞት አደጋ ሊከሰት ይችላል፡፡
===የተነደፈው ሰው ከሚከተሉት ነገሮች መቆጠብ አለበት===
>> ከአልኮል እና ሲጋራ፣
>> ህመምን ሊቀንሱ ከሚችሉ እንደ ሞርፊን ያሉ መድኃኒቶች፣
>> አይንን በእጅ ከመነካካት(አነስተኛ መጠን ያለው መርዝ ወደ ዓይናችን ከገባ፣ አይናችንን ሊያጠፋ ይችላል፡፡)
>> የተነደፈውን አካባቢ እብጠት ከማሻሸት መቆጠብ አለበት፡፡
ከዚህ በላይ በተመለከትናቸው ዘዴዎች መርዙን ካወጣን በኋላ፡-
>> ቁስለቱ እንዳያመረቅዝ ማፅዳትና አየር እንዲያገኝ ማድረግ፣
>> ቁስለቱን በንፁህ ጨርቅ መሸፈን፣
>> ተጎጂው ብዙ ፈሳሽ እንዲጠጣ ማድረግ አለብን፡፡
መላ፡- ቁስለቶችን ለማፅዳት ውኃ ማግኘት የማንችል ከሆነ ሽንታችንን ልንጠቀም እንችላለን፡፡
●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●
→ ምንጭ ፦ SURVIVAL 101
→ አቅራቢ ፦ አብዲ ሸሪፍ ኑር

0 1652

 

ውድ አንባብያን እንደምን ከረማችሁ? ዛሬ ይህ እፁብ ድንቅ የሆነውን አካላችንን የልጅ መልክ እንዲኖረው የሚያደርግ አንድ ምስጢር ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡

አንድ ጥያቄ ላስቀድም፡፡ ይሄ የእኛ አካል ከምንድን ነው የተሰራው ብላችሁ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?  እንግዲህ ‹‹የእርጅና መድሃኒትን›› ማወቅ ከፈለጋችሁ ከዚህ በታች በማብራራው ጉዳይ ላይ ትዕግስት እንዲኖራችሁ ከወዲሁ እጠይቃለሁ፡፡ በተቻለኝ መጠን ነገሮችን ሳላወሳስብ አንድ መሰረታዊ የሆነን የሳይንስ ግንዛቤን ለማብራራት እሞክራለሁ፡፡

የሰው ልጅ አካል የተሰራው በዋነኝነት ከፕሮቲን ነው፡፡ ፕሮቲን ደግሞ የተገነባው ቢያንስ ከአምስት መሰረታዊ ንጥረ ነገሮች ነው፡፡ ይኸውም ካርቦን (C)፣ ሃይድሮጅን (H)፣ ኦክሲጂን (O)፣ ናይትሮጂን (N) እና ሰልፈር (S) ናቸው፡፡ እነዚህ ንጥረ ነገሮች ደግሞ በአየር፣ በውሃ፣ በአፈር፣ በእፀዋትና፣ በእንስሳት ውስጥ በተለያየ መጠን ይገኛሉ፡፡ ሕይወት እንዴት እንደተሳሰረ ተመለከታችሁ? ይሄ ማለት ወደ ተፈጥሮ ስር መሰረት ስሪት ስንመለስ ህይወት ያለውም ሕይወት የሌለውም አንድ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው እና መሰል ንጥረ ነገሮች (የካርቦን፣ ኦክስጂን፣ ሃይድሮጂን ወዘተ…) በቀላል ቋንቋ አተም እንላቸዋለን፡፡ አተሞች የተሰሩት ደግሞ ከሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ነው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ኤሌክትሮን ይባላል፡፡ እነዚህ ንጥረ ነገሮች እርስ በእርስ እየተሳሳቡና እየተጣመዱ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ይፈጥራሉ፡፡ ለምሳሌ ፕሮቲን፣ ስብ፣ ውሃ፣ አልኮል፣ ነዳጅ ወዘተ…፡፡

በአተሞች የላይኛው ምህዋራቸው ላይ የሚሽከረከሩት ኤሌክትሮኖች በባህሪያቸው በሁለት ይከፈላሉ፡፡ ቁጥራቸው 8 ከሆነ የተረጋጉ (Stable) ይሆናሉ፡፡ ሰባትና ከዚያ በታች ሲሆኑ ደግሞ ያልተረጋጉ (Unstable) ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ እነዚህ ያልተረጋጉ አተሞች ሁልጊዜ የህይወት ትግላቸው ለመረጋጋት የሚያስችላቸውን ተጨማሪ ኤሌክትሮን መፈለግ ነው፡፡ ይሄንን ተጨማሪ ኤሌክትሮን አንድ በመበደር ወይም በመጋራት አለዚያ አለመረጋጋቱን የፈጠረውን ትርፍ ኤሌክትሮን በማበደር ከሌሎች አተሞች ጋር ጥምረት በመፍጠር ለመረጋጋት ይሞክራሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ የህይወት ቅምር ሰንሰለት ሒደቱን ይቀጥላል፡፡ ይሄ ግንዛቤ ቀጥሎ ለማስረዳው ጉዳይ መሰረት ነው፡፡

የአካላችን ግንባታ የሚጀምረው ከሴሎች ነው (ሴሎች የተሰሩት ከላይ ከጠቀስናቸው ንጥረ ነገሮች መሆኑን አስታውሱ)፡፡ ልክ ቤት ሲሰራ ከብሎኬት ወይም ከጡብ እንደሆነ ሁሉ ማለት ነው፡፡ (ጡብና ብሎኬቱ የተሰሩት ደግሞ ከተለያዩ ግብዓቶች ነው)፡፡ ሴሎች በዓይን የማይታዩ ህዋሶች ናቸው፡፡ እነርሱ ተገጣጥመው ግን ቲሹ (Tissue) ይሰራሉ፡፡ ቲሹን እንደ የቤቱ የአንድ ጎን ግድግዳ እንመልከተው፡፡ ገና ቤት አልሆነም፡፡ ቲሹዎች ተገጣጥመው ደግሞ የአካላችንን የተለያዩ ክፍሎችን ይሰራሉ፡፡ ለምሳሌ፣ ዓይን፣ አፍንጫ፣ ሣንባ፣ ጉበት፣ ልብ ወዘተ…፡፡ እነዚህ ክፍሎች ደግሞ በተለያዩ ስርዓቶች (Systems) ተያይዘው የሰውን አካል ሙሉውን ይሰራሉ ማለት ነው፡፡

ይሄ አካል እንግዲህ በብዙ ትሪሊዮኖች ከሚቆጠሩ ሴሎች ነው የተገነባው፡፡ እነዚህ ሴሎች እያንዳንዳቸው ለራሳቸው የሚሆን ኃይል (Energy) ማመንጨት ይችላሉ፡፡ ይህ ደግሞ የሚሆነው ከምግብ የሚገኘውን የኃይል ምንጭ የሆነውን ግሉኮስ እንደማገዶ ሰባብሮ ወደ ኤቲፒ (ATP) የሚባል የኃይል ቅምር ወይም በቀላል አማርኛ የባትሪ ድንጋይ በመቀየር ነው፡፡ ይሄ ሂደት እያንዳንዷን ሴል በህይወት እንድትቆይ ያደርጋል፡፡

ሴሎች ከላይ የተብራራውን እጅግ በጣም አስፈላጊ ስራ ሲሰሩ በጎንዮሽ በጣም አጥፊ የሆኑ ኬሚካሎች ይፈጠራሉ፡፡ ስማቸውም ፍሪ ራዲካልስ (Free Radicals) ይባላል፡፡ ፍሪ ራዲካሎች በተፈጥሮ የሚኖሩያልተረጋጉ የኦክሲጅን አተሞች ናቸው፡፡ ይህ አለመረጋጋታቸው ደግሞ ሁልጊዜ የጎደላቸውን ኤሌክትሮን ለማሟላትና ለመረጋጋት ሲሉ አንድ እጅግ አደገኛ የሆነ ስራ ይሰራሉ፡፡ ይህም ራሳቸውን እየወረወሩ ተረጋግተው ስራቸውን ከሚሰሩት ሴሎቻችን ጋር እያጋጩ ኤሌክትሮን ለመስረቅ ትግል ይጀምራሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሳቢያ ይሄንን ውርጅብኝ የሚቀበሉ ሴሎቻችን ላይ ጉዳት ይደርሳል፡፡ ጉዳቱ ሴሎች ዳግመኛ በትክክል እንዳይሰሩ ከማድረግ በተጨማሪ በትክክል እንዳይራቡ የዘር ስሌትን እስከ መጉዳት (Genetic Matrial Damage) ሁሉ ሊያደርስ ይችላል፡፡

ይሄ የፍሪ ራዲካሎች ጦርነት እወጃ ሴሎቻችንን በጎዳ ቁጥር የእኛም ቆዳና አካል እያረጀ ይሄዳል፡፡ ማርጀት ብቻ ሳይሆን የፍሪ ራዲካሎች ጥቃት ከዚህም የከፋና ቁጥራቸው በርካታ ለሆኑ የጤና ችግሮች አካላችንን ያጋልጣል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የፍሪ ራዲካሎች ቁጥር በአካላችን ውስጥ መብዛትና የካንሰር በሽታ መፈጠር በከፍተኛ ደረጃ ተዛማጅነት አላቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለሌሎች በሽታዎች ማለትም ለልብ በሽታ፣ ለደም ስሮች መቆርፈድ፣ የደም መርጋት፣ ኢንፍላሜሽኖች (ለካንሰር መንሰራራት መንስኤ ነው)፣ ለቆዳ ጉዳት ወዘተ… መንስኤ ይሆናል፡፡

ከላይ እንደተገለፀው እንግዲህ ይነስም ይብዛም ይሄ በተፈጥሮ ፍሪ ራዲካሎችን እንደ የጎንዮሽ ውጤት የማምረቱ ሂደት በሁላችንም አካል ውስጥ አለ፡፡ ጥቁር ይሁን ነጭ፣ ቀይ ይሁን ቢጫ የተባለ የሰው ዘር ውስጥ ሁሉ የሚገኝ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ግን ይሄን የፍሪ ራዲካሎችን ምርት የሚያባብሱ ነገሮች አሉ፡፡ እነርሱም ሲጃራ ማጤስ፣ መጠጥ መጠጣት፣ የአየር ብክለት (በተለያዩ ኬሚካሎች)፣ የተጠበሱ ስብና ቅባት የበዛባቸው ምግቦች፣ በጣም ጣፋጭ ምግቦች፣ አርቴፊሻል ማጣፈጫዎች፣ እና ቀለሞች ወዘተ… ያሉባቸው ምግቦች እና የመሳሰሉት እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት አካላችንን የሚጎዱ ነገሮች ወደ ሰውነታችን ሲገቡ ሰውነት እነርሱ የያዙትን መርዝ (Toxin) ለማስወገድ በሚታገልበት ጊዜ በርካታ ፍሪ ራዲካሎች ይመረታሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ የሚፈጠሩት ፍሪ ራዲካሎች ደግሞ ቁጥራቸው እጅግ በርካታ ከመሆኑ በተጨማሪ ጉዳታቸውም በተፈጥሮ ከሚመረቱት ፍሪ ራዲካሎች የከፋ ነው፡፡ ለዚህ ነው የአልኮል ጠጪዎች፣ ሲጃራ አጫሾች፣ የጫትና የሺሻ ወዘተ… ሱሰኞች ከእኩዮቻቸው ቶሎ የፊት ቆዳቸው ሲያረጅና አካላቸው ሲላሽቅ የምናየው፡፡ የልጅ መልክ የነበራቸው ሰዎች በእነዚህ ሱሶች ሲጠመዱ ወዲያውኑ በተለይ የፊት ቆዳቸው በዓይናቸው ዙሪያ ያለው ስስ ቆዳ የመጥቆርና የመሸብሸብ ምልክት ያሳያል፡፡ ይህ እንግዲህ ከውስጥ የሚፈጠረውን ጉዳት የማይጨምር ነው፡፡

እንግዲህ ወገኖቼ እዚህ ላይ ቆም ተብሎ ሊታሰብ ይገባል፡፡ በሰውነታችን ውስጥ በተፈጥሮ የሚፈጠሩት ፍሪ ራዲካሎች ሳያንሱ ከውጭ እያመጣን በምንሞጅራቸው መርዞች አማካኝነት ለምን ለተጨማሪ ጉዳት ራሳችንን እናጋልጣለን? ስለዚህ ቢያንስ የፍሪ ራዲካሎችን ምርት ሙሉ ለሙሉ ማስቆም ባይቻል እንኳ በከፍተኛ መጠን ግን መቀነስ እንችላለን፡፡ በተፈጥሮ የሚፈጠሩትን ከስር ከስር ማስወገድ ራሱ በቂ የቤት ስራ ነው፡፡

ፍሪ ራዲካሎች ከሰውነታችን እንዴት እናስወግድ?

‹‹ሳይደግስ አይጣላም›› እንዲሉ ለፍሪ ራዲካሎች የሚሆኑ አስገራሚ መድሃኒቶች አሉ፡፡ ፍሪ ራዲካሎች ሴሎቻችንን እንዳይጎዱ እንደ ጋሻ እየተከላከሉ እና እንዲረጋጉ ደግሞ የሚፈልጉትን ኤሌክትሮኖች የሚለግሱ ማለት ነው፡፡ እነዚህ ነፃ አውጪዎች ደግሞ ምንድን ናቸው? አትሉም፡፡ እነዚህ ነፃ አውጪዎች ስማቸው ‹ሚ‹አንታይ ኦክሲዳት›› ይባላል፡፡ የኬሚካል ስሞች እንደበዛባችሁ ይገባኛል፡፡ ነገር ግን ይሄንን ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ወደ አማርኛ ለመተርጎም ብንሞክር ሌላ የአማርኛ ፍቺ የሚጠይቅ የአማርኛ ቃል እንዳይሆንብን እሰጋለሁ፡፡ ስለዚህ ልክ የውጭ ሀገር የእግርኳስ ተጨዋቾችን ስም እንደምንሸመድደው እነዚህንም በቃላችን እንያዛቸው፡፡ ደጋግመን አንብበንም እናጥናቸው፡፡ ይሄ ጉዳይ የእያንዳንዳችን አካል ጉዳይ ነውና፡፡

አንታይ ኦክሲዳንቶች ከላይ እንደገለፅኩት በተፈጥረአቸው ትርፍ ኤሌክትሮን ለጋሾች ናቸው፡፡ ትርፍ ኤሌክትሮኖችን ለእነዚያ ኤሌክትሮን ተርበው ሴሎቻችንን ለሚወግሩት ፍሪ ራዲካሎች በመስጠት ያረጋጓቸዋል፡፡

ታዲያ አንታይ ኦክሲዳንቶችን ከየት ነው የምናገኛቸው? የሚል ጥያቄ ካነሳን በአንድ በኩል በመጠኑ ሰውነታችን ራሱ የሚያመርታቸው ሲሆን በሌላ በኩል ግን በበቂ መጠን በምግባችን አማካኝነት ለሰውነታችን መቅረብ አለበት፡፡

አንታይ ኦክሲዳንቶች እስከ ዛሬ በተደጋጋሚ እንደተገለፀው በብዛት የሚገኙት በአትክልትና ፍራፍሬ ውስጥ ሲሆን በተጨማሪ ከተለያዩ እርጥብና ደረቅ ቅመሞችና እንደ የወይራ ዘይት አይነት ጤናማ ቅባቶች ውስጥም ይገኛሉ፡፡

የሚገርማችሁ አንታይ ኦክሲዳንቶች ያለባቸውን ምግቦች ለይቶ መሸመት እጅግ በጣም ቀላል ከመሆኑ የተነሳ ምንም ያልተማረ ሰው እንኳን እየለቀመ ሊያወጣቸው ይችላል፡፡ ይኸውም ቀለማቸውን በማየት ነው፡፡

አንታይ ኦክሲዳንት ያለባቸው ምግቦች በአብዛኛው በቀለም ኮዳቸው ይመደባሉ፡፡ እነርሱም ቀያዮቹ፣ ቢጫና ብርቱካናማዎቹ፣ አረንጓዴዎቹ፣ ወይን ጠጅና ሰማያዎቹ፣ ነጭና ቡናማዎቹ ወዘተ… በመባል ነው፡፡

ቀያዮቹ

ቀያዮቹ አትክልትና ፍራፍሬዎች በውስጣቸው ላይኮፔን (Lycopen) የሚባል አንታይ ኦክሲዳንት የያዙ ሲሆን ለቀለማቸው ቀይ መሆን ምክንያትም ነው፡፡ ቀያዮቹን ለመጥቀስ ያህል ቲማቲም፣ ሐብሐብ፣ እንጀራ፣ የሮማን ፍሬ፣ ቀይ አፕል፣ ራድሽ (የቀይ ስር ዘሮች ሆነው ትንንሽ ናቸው)፣ ፕሪም፣ የፈረንጅ ቀዩ ቃሪያ፣ ቀይ ቦለቄ ወዘተ…፡፡

ቢጫና ብርቱካናማዎቹ

እነዚህ ደግሞ በውስጣቸው ቤታ ካሮቲንና አስኮርቢክ አሲድን (Beta Carotene and Ascotic Acid) የመሳሰሉት የአንታይ ኦክሲዳንት አይነቶችን የያዙ ሲሆን በተለምዶ ቫይታሚን ኤ እና ቫይታሚን ሲ በምሳሌነት ይነሳሉ፡፡ ለአብነት ያህል ለመጥቀስ ብርቱካን፣ አናናስ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ካሮት፣ ዱባ፣ ቢጫውና ብርቱካናማው የፈረጅን ቃሪያ ወዘተ… ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ወይን ጠጅና ሰማያዊዎቹ

እነዚህኞቹ ደግሞ አንቶሳይኒን (Anthocyanin) እና ፍላቫኖይድ (Flavanoids) የሚባሉትን የአንታይ ኦክሲዳንት ዓይነት የያዙ ሲሆን እንደ ብሎቤሪ፣ ብላክቤሪ፣ ወይን ጠጅ ካሮት፣ ወይን ጠጅ አበባ፣ ወይን ጠጅ ጎመን፣ ወይን ጠጅ ድንች ያሉ እኛ ሀገር የማይገኙ ይሄንን አይነት አንታይ ኦክሲዳንቶች በብዛት የያዙ ፍራፍሬ እና አትክልት ናቸው፡፡ እኛ ሀገር ከሚገኙት መካከል ብርንጃል፣ ወይን ጠጅ ጥቅል ጎመን፣ ወይን ጠጅ የፈረጅን ቃሪያ፣ ወይን ጠጅ ወይን፣ ቀይ ስር፣ ወይን ጠጅ ቀይ ሽንኩርት (በተለምዶ ቀይ ሽንኩርት የሚባለው) ይጠቀሳሉ፡፡

አረንጓዴዎቹ

አረንጓዴዎቹ ደግሞ በዋናነት ሎቲን እና ዚያክሳንቲን (Lutein and Zeaxanthin) የተባሉትን የአንታይ ኦክሲዳንት አይነቶችን የያዙ ሲሆን ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ብሮክሊ፣ ስፒናች፣ አስፓርገስ፣ ቆስጣ፣ ሰላጣ፣ ጎመን፣ ቃሪያ፣ ፎሶሊያ፣ አረንጓዴ የፈረንጅ ቃሪያ፣ አረንጓዴ አፕል፣ የድንብላል ቅጠል፣ የስጎ ቅጠል፣ የጥብስ ቅጠል፣ ኮሰረት፣ ጦስኝ፣ በሶብላ፣ ወዘተ… ይጠቀሳሉ፡፡

ነጫጮቹና ቡናማዎቹ

እነዚህኞቹ ደግሞ አሊሲን (Allicin) እና ኪውርሲቲን (Quercetin) የተባሉትን አንታይ ኦክሲዳንቶች ይይዛሉ፡፡ እነዚህ አንታይ ኦክሲዳንት ነጭ ሽንኩርት፣ አበባ ጎመን፣ እንጉዳይ፣ ነጭ ቦለቄ፣ ነጭ ራዲሽ (ነጭ ካሮት የሚመስል)፣ የተፈጥሮ ካካዎ፣ ተልባ፣ አጃ ወዘተ… ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ በዚህ መልኩ ከተረዳነው በቀላሉ ሸምተን በገበታችን ላይ እንዲገኙ ማድረግ እንችላለን፡፡ እዚህ ላይ ላስገነዝብ የምፈልገው ከላይ የቀረበው አይነት አከፋፈል እንዲህ በቀላሉ አንታይ ኦክሲዳንቶቹን ለመረዳት እና ለመለየት እንዲያስችል ሆኖ የተዘጋጀና የአንታይ ኦክሲዳንቱ አይነት በጣም ጎልቶ በብዛት በሚገኘው ተመድቦ እንጂ በአንድ ቡድን ውስጥ ሌላው አይነት አንታይ ኦክሲዳንት ፈፅሞ አይገኝም ማለት አይደለም፡፡ ያው እንደምታውቁት ተፈጥሮ በቸርነት የተገነባች ነች፡፡ ተፈጥሮ ላይ አንድ ሲደመር አንድ ሁለት ብቻ ነው የሚባል ነገር የለም፡፡ ነገር ግን እንዳያችሁት እንደዚህ በቀለም ከፋፍለን ስናየው ብዙ ስራ ያቃልልልናል፡፡ በቀላሉ ያግባባናልም፡፡

ማስታወሻ

አንታይ ኦክሲዳንቶችን በተጨማሪ ምግብነት (Food Supplements) ተዘጋጅተው ቫይታሚን ኤ፣ ቫይታሚን ሲ፣ ቫይታሚን ኢ ወዘተ… በመባል የሚቀረቡበት ሁኔታ አለ፡፡ ነገር ግን አንድን አይነት ንጥረ ነገር ለብቻው ነጥሎ አውጥቶ መጠቀምን የስነ ምግብ ሳይንቲስቶች አይመክሩም፡፡ የተሻለ የሚሆነው እነዚህን አንታይ ኦክሲዳንቶችን ከላይ ከተዘረዘሩት የተፈጥሮ ምግቦች ብናገኛቸው ነው፡፡ ለዚህም የሚያቀርቡት ምክንያት፣ አንታይ ኦክሲዳንቶች ለፍሪ ራዲካሎች ኤሌክትሮን ከለገሱ በኋላ ራሳቸውን እንዲያረጋጉ የሚያደርጉ ሌሎች አንታይ ኦክሲዳንቶች በምግቡ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ይህም የኤሌክትሮን እጦት የሚፈጥረውን ሠንሠለታዊ ሂደቶችን (Chain Reactions) እንዳይኖር ይረዳሉ፡፡ በአርቴፊሻል መንገድ አንድ አይነት አንታይ ኦክሲዳንትን ነጥለን ብንወስድ ግን ይሄን አይነት ድጋፍ አናገኘም፡፡

በመጨረሻም ‹‹በቂ አንታይ ኦክሲዳንት ያለበትን ምግብ እየበላሁ እንደሆነ በምን አውቃለሁ?›› ብሎ ለሚጠይቅ፣ የማዕዳችሁን ቀለም ተመልከቱ እላለሁ፡፡ በተለይ በተለይ ምግባችን በእሳት ያልተጎዳ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በየዕለቱ የምንመገበው ከሆነ ጥሩ የአንታይ ኦክሲዳንት ማዕድ እንደሆነ ማረጋገጫ ነው፡፡

ስለዚህ ምግባችንን በእነዚህ ደማቅ ቀለሞች በታጀቡ ምግቦች በማስዋብ ወጣት እንደመሰልን እንድናረጅ እየመከርኩ ለዛሬ በዚሁ ልሰናበት፡፡

source -zehabesha

 

0 586

ጥርስን መጠበቅ
የታችኛው መንጋጋ ትንንሽ ጥርሶች እንደተለመደው መጀመሪያ ይወጣሉ። ይሄም የሚከሰተው  ከስድስት እስከ ስምንት ወራት እስኪሆነን ነው። ነገር ግን ቀድመውም ሆነ ዘግይተው ሊወጡ ይችላሉ። ከዚያ ቀጥለው የሚወጡት የላይኛው መንጋጋ የፊት ጥርሶች ሲሆኑ በመከተልም የፊት ጥርሶች፣ ክራንቻ እና በመጨረሻም የኋላኞቹ የመንጋጋ ጥርሶች ይወጣሉ። በአብዛኛው ልጆች እድሜያቸው ከሁለት ተኩል እስከ ሶስት አመት ሲሆናቸው ሁሉንም የወተት ጥርሶች ማለትም አስር ከላይ አስር ከታች ያበቅላሉ።

የጥርስ መቦርቦር
ስኳር ለጥርስ መቦርቦር ምክኒያቱ ነው። ልጆች ስኳር አዘል የሆነ ምግብ ስንበላ ወይም ስንጠጣ በአፍ ውስጥ ያለው ባክቴሪ አሲድ በማመንጨት ጥርስ እንዲበሮቦር ያደርጋል።  ስለዚህም ከመመገቢያ ሰአት ውጪ ስኳር የያዘ ነገር ያለመብላት ወይም ያለመጠጣት ጥሩ ነው።

ጥርሳችንን ማፅዳት
ከጫወታ ወደ ቁም ነገር ፤ የመጀመሪያ ጥርስ በትንሽ እና ለስላሳ የጥርስ ብሩሽ ማፅዳት ይችላል። ጥርስ መቦረሹን እንደ ጨዋታ መጀመር ይቻላል። ጥርሳችንን በቀን ሁለት ጊዜ በጥርስ ሳሙና መፋቅ አለብን፡

ጣፋጭ ምግብ መቀነስ
ጥሩ ምግብ እና የአመጋገብ ባህሪይ ለጥርስ ብቻ ሳይሆን ለመላው አካል አስፈላጊ ነው።  ጣፋጭ ነገሮች ቅዳሜ እና የተለየ ዝግጅት ለምሳሌ ልደት ሲኖር ብቻ ብንመገብ መልካም ነው። እንደ አፕል፣
ካሮት የመሳሰለ መስጠት ለጥርስም ለሰውነትም ጥሩ ነው።

አደጋ ከደረሰ
ልጆች በአጋጣሚ ከወደቅን ወይም አፋችን ሲመታ አንዱ  ወይም ብዙ ጥርሶች ሊጎዱ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ በአከባቢያችን ወደሚገኝ  የጥርስ ክሊኒክ ወይም የህክምና ተቋም መሄድ አለብን።

 Source; akukulunews

0 730

የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ለማስወገድ ይረዳል፡፡
• የቆዳ ድርቀትን ይከላከላል፡፡
• ጥሬ ፓፓያ ፊትዎን ለ 25 ደቂቃ በመቀባት ፊት ላይ የሚገኙ ጥቃቅን ያበጡ
ነጠብጣቦችን በቀላሉ ማስወገድ ይችላሉ፡፡
• ፓፓያን በቀጥታ ቆዳዎን በመቀባት ወይም በመመገብ የሚያምር ለስላሳ
ቆዳን መጎናፀፍ ይቻላሉ፡፡
• የተፈጨ ፓፓያ የተሰነጣጠቀ ተረከዝን ለማከም ይጠቅማል፡፡
• ተፈጥሮአዊ የሞቱ ሴሎችን ከቆዳ ላይ ማስወገጃ መንገድ ነው፡፡
• የቆዳን ተፈጥሮአዊ ቀለም ለመመለስ ይረዳል፡፡
• ለሆድ ትላትል ህክምናነት ይጠቅማል፡፡
• በቆዳ ላይ የሚታዩ የእርጅና ምልክቶችን ለመቀነስና ለማከም ይረዳል፡፡
• ጥቁር ነጠብጣቦችን ለማስወገድ ይረዳል፡፡
• ራሰ በራነትን ይከላከላል፣ የፀጉር እድገትንና ጥንካሬን ይጨምራል፡፡

መልካም ጤንነት!!12733466_571455373009087_5923322859486672542_n

0 1054

በማስረሻ መሀመድ

ጄንጅቫይትስ (የድድ እንፌክሽን) ብዙ ጊዜ የሚከሰት የድድ/የጥርስ ዙሪያ ላይ ህመም ሲሆን መቆጥቆጥ፣ ቅላትና እብጠት በድድዎ ላይ እንዲከሰት ያደርጋል:: ብዙዉን ጊዜ ህመሙ መጠነኛ የሆነ ምልክት ስለሆነ ያለዉ ታማሚዉ ሳያስተዉለዉ ሊያልፍ ይችላል::

የህመሙ ምልክቶች፡ ጤናማ ድድ ጠንካራና ቀላ ያለ ሮዝ ቀለም ያለዉ ሲሆን የድድ ላይ ህመም ሲከሰት የሚከተሉትን ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል:: እነርሱም • የድድ እብጠት

• ልልና የተነፋ ድድ

• አንዳንዴ ሲነካ ህመም መኖር

• ጥርስዎን በሚፍቁበት/በሚቦርሹበት ወቅት በቀላሉ መድማት

• የድድዎ መልክ መቀየር(ከጤናማ ቀይ ወደ ደበዘዘ ቀይ)

• መጥፎ የአፍ ጠረን መከሰት ናቸዉ

የህመሙ ምክንያቶች

ጄንጅቫይትስ በብዛት የሚከሰተዉ የአፍ ዉስጥ ንፅህናን በደንብ በማይጠብቁና በዚህ የተነሳ በድድና ጥርስ ላይ የሚጋገር ነገር/ plaque/ እንዲፈጠር እድል የሚፈጥሩት ሰዎች ላይ ነዉ:: ይህ የተጋገረዉ ነገር በዐይን የማይታዩ ባክቴሪያዎችን የያዘ ነዉ::

ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች

የድድ ችግር በማንኛዉም ሰዉ ላይ ሊከሰት የሚችል ነዉ:: ነገር ግን ተጋላጭነትዎን ከሚጨምሩ ነገሮች ዉስጥ

• የአፍ ጤንነታቸዉን/ ንፅህናቸዉን በደንብ በማይጠብቁ

• ሲጋራ በሚያጨሱ ሰዎች ላይ • የስኳር ህመም

• በእርጅና እድሜ ወቅት

• መድሃኒቶች

• የአፍ ድርቀት

• የሆርሞን ለዉጥ( በተለይ በሴቶች ላይ እርግዝና፣ በወር አበባና የእርግዝና መከላከያ እንክብል በሚወስዱበት ወቅት)

• ጥሩ አመጋገብ ከሌለዎ እና
• አደንዛዥ ዕፅ የሚጠቀሙ ከሆነ ነዉ::

ሊደረግ የሚችል ህክምና

ለህመሙ የሚደረግ ህክምና የህመም ምልክቶቹን ከመቀነስ ባሻገር ህመሙ ወደከፋ ደረጃ እንዳይሄድና የጥርስ መዉለቅን ሊከላከል ይችላል:: ዉጤታማ ህክምና ለማግኘት የባለሙያ ክትትልና ከህመሙ በኃላ የአፍ ዉስጥ ንፅህናን መጠበቅ ያስፈልጋል::

የቤት ዉስጥ ህክምናና የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ • የጥርስ ህክምና ባለሙያዉ በሚያዘዉ

መሰረት መደበኛ የሆነ የጥርስ እጥበት ማካሄድ • ለስለስ ያለ የጥርስ ቡርሽ መጠቀምና ቢያንስ በየሦስትና አራት ወራት መቀየር • በቀን ሁለቴ አሊያም ከእያንዳንዱ ምግብ መርሃግብር በኃላ አፍዎን ማፅዳት • የጥርስ ህክምና ባለሙያዎ ካዘዘልዎ የጥርስ ማጠቢያ አንቲሴፕቲክ መጠቀም • በጥርስ መካከል ለማፅዳት ተብለዉ የተዘጋጁ የጥርስ መጎርጎሩያ/ዴንታል ፒክ መጠቀም::
source-zehabesha

0 1167

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር )

የማይግሬን ራስምታት በሚነሳበት ጊዜ ህመሙን ለማስታገስ የሚጠቅሙ ሁኔታዎችን እገልጽላችኋለሁ፡፡
1. የተረጋጋ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይምረጡ
✔ በአካባቢዎ የሚገኝ መብራት ማጥፋት እና ከተቻለ እንቅልፍ መተኛት፣
✔ የሞቀ ወይንም የቀዘቀዘ ውኃን በላስቲክ በማድረግ በእራስዎ እና በአንገትዎ ላይ ማስቀመጥ፣ ይህ ማለት ደግሞ
• ቅዝቃዜው በማደንዘዝ ሕመም እንዳይሰማዎ ሲያደርግ ሙቀቱ ደግሞ የራስና የአንገት ጡንቻዎችን እንዲፈታቱ ያደርጋል
• ሕመም የሚሰማዎ ቦታ ላይ በቀላሉ ማሸት አንገትዎን እና ትከሻዎን ማሸት
✔ ገላዎን በሙቅ ውሀ መታጠብ
2. በቂ እረፍት ማድረግ
✔ መደበኛ የእንቅልፍ ሰዓት ይኑርዎ
✔ ሁሌም በተመሳሳይ ሰዓት የመተኛት ልምድ ያዳብሩ
✔ በቀን እንቅልፍ መተኛት ያስለመዱ ከሆነ ከ20-30 ደቂቃ ብቻ ቢሆን ይመከራል። ከዛ በላይ እንቅልፍ ከወሰዱ የለሊት እንቅልፍዎን ሊያዛባ ይችላል
✔ እንቅልፍዎ ያልመጣ ከሆነ እራስዎን አያስገድዱ መጽሐፍ በማንበብ ራስዎን ያድክሙ
3. አመጋገብዎን ያስተካክሉ
✔ መደበኛ የሆነ የምግብ ሰዓት ይኑርዎ
✔ ቁርስዎን መመገብ አይዘንጉ
✔ ማይግሬን ቀስቃሽ የሆኑ ምግቦችን ያስወግዱ (እንደ ቼኮሌት፣አይብ፣ቡና እና የአልኮል መጠጦች)
4. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል ነገር ግን ሐኪምዎን በማማከር ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ
(ለምሳሌ እንደ ውሃ ዋና፤የእግር ጉዞ የመሳሰሉትን ማድረግ ይችላሉ)
5.ጭንቀትዎን ይቆጣጠሩ
ጭንቀት የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል፡፡ በዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታዎች የሚያጋጥሙንን አስጨናቂ ነገሮች መከላከል ባይቻልም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በመፈፀም መቀነስ ይችላሉ።
✔ ቀለል ያለ የኑሮ ዘይቤ ይኑርዎ
✔ ጊዜዎን በአግባቡ ይጠቀሙ
✔ የዕረፍት ጊዜ ይኑርዎ
✔ ለነገሮች በጎ አመለካከት ይኑርዎ
✔ ራስዎን ዘና ያድርጉ
6. የራስ ምታትዎን በተመለከተ የግል ማኅደር ይኑርዎ
✔ በግል ማኅደር መመዝገብ ራስምታትዎን የሚያስነሳውን ሁኔታ ለማወቅ እና ምን እንደሚያስታግስልዎም ለማጤን ይረዳል፡፡
ጤና ይስጥልኝ

source -zehabesha

0 1164

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

1. በነጭ ሽንኩርት ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር በፈንገስ ምክንያት ለሚከሰቱ የቆዳ ሕመሞች መድኃኒትነት አለው፡፡
2. በከፍተኛን ደረጃ ባክቴሪያንና ቫይረሶችን የማጥፋት ብቃት ያለው የምግብ ዓይነት ነው፡፡
3. ነጭ ሽንኩርት በውስጡ የደም መርጋትን የሚከላከል ንጥረ ነገርን ይይዛል፡፡
የደም ግፊት መጨመርን ይከላከላል፡፡
4. ከዕድሜ መጨመር የተነሳ የሚከሰት የደም ቧንቧ ጥበትን የመከላከል ጥቅም ያለው ነጭ ሽንኩርት ይህንን በማድረግ በደም ቧንቧ ጥበት ምክንያት የሚከሰት የልብ ሕመምን ይከላከላል፡፡
5. በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የኮሌስትሮል መጠን በመቀነስ በደም ቧንቧ ላይ የሚገኘውን የስብ መጠን እንዲቀንስ ያድርጋል፡፡
6. ሰውነታችን በአለርጂ እንዳይጠቃ የማድረግ አቅምም አለው፡፡ በሰውነት ላይ ለሚወጣ ሽፍታና በአንዳንድ ነፍሳት ምክንያት የሚወጣንን ሽፍታም ይከላከላል፡፡
7. ነጭ ሽንኩርት በጉንፋን የመያዝ ሁኔታን በከፍተኛ ደረጃም ይቀንሳል፡፡ከተያዝንም በኋላ እንዳይበረታብንና ቶሎም እንድንድን ይረዳል፡፡
8. ነጭ ሽንኩርት በሰውነታችን የሚመነጨውን የኢንሱሊን መጠን መጨመርና በደም ውስጥ የሚገኙትን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ለስኳር ሕመም ጠቀሜታነት ይሰጣል፡፡
9. የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት ጥርሳችንን በሚያመን ቦታ ላይ በማድረግ ባክቴሪያዎችን ማጥፋትና ሕመምን የመቀነስ ጥቀም አለው፡፡
ጤና ይስጥልኝ
source=zehabesha