ሐዲስ

0 359

تَعَالىَ طَيَّبٌ لايَقْبَلُ إلاَّ طَيَّبَّا،  وإنَّ الله أَمَرَ الُمؤْمِنينَ بمَا أَمَرَبهِ المُرْسَلينِ فقاَلَ تَعَالَى (يَا أَيُّها الرُّسُلُ كُلُوا مِنَ الطَّيَّبَاتِ واعْمَلُوا صَاِلحاً) وقَالَ تَعَالَى (يَاأَيُّها الَّذِينَ آمَنُوا كُلُوا مِنْ طَيَّبَاتِ مَارَزَقْنَاكُمْ) ثُمَّ ذَكَرَ الرَّجُلَ يُطِيلُ السَّفَرَ أَشْعَثَ أَغْبَرَ يَمُدُّ يَدَيِه إلى السَّمَاءِ : يَارَبُّ يَارَبُّ، ومَطْعَمُهُ حَرَامٌ ومَشْرَبُهُ حَرَامٌ ومَلْبَسَهُ حَرَامٌ وغُذِىَ بالْحَرام فَأَنىَّ بُسْتَجَابُ لَه. رَوَاهُ مُسْلِمٌ

 

ከአቢ ሁረይራ (ረ.ዐ) የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፡-

‹ልዑል የሆነው አላህ ጥሩ ነውና ጥሩን ነገር እንጂ አይቀበልም፡፡ አላህ መልዕክተኞችን ባዘዘበት ነገር ምእመናንንም አዟል፡፡ ልዑል የሆነው አላህ እንዲህ ብሏል ‹እናንተ መልዕክተኞች ሆይ! ከጥሩ ነገሮች ብሉ፣ በጐ ሥራንም ሥሩ…» (አል-ሙእምኑን፡ ቁ-51) እንዲሁም «እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ ከሰጠናችሁ ጣፋጮች ብሉ…» (አል-በቀረህ ቁ፡ 172) ፡፡ ከዚያም ስለአንድ በረጅም ጉዞ ላይ ያለ፣ ፀጉሩ የተንጨበረረና በአቧራ የተሸፈነ ሰው አወሱ፡፡ እጁን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ጌታዬ ሆይ! ጌታዬ ሆይ! ይላል፡፡ የሚመገበው ሐራም፣ የሚጠጣው ሐራም፣ የሚለብሰው ሐራም፣  ያደገውም በሐራም ነው፡፡ ታዲያ እንዴት ዱዓው ተቀባይነት ያገኛል? ሲሉ ተናገሩ፡፡›   (ሙስሊም ዘግበውታል፡፡)

አምላካችን አላህ (ሱ.ወ.) በምሉእነት ባህሪው ብቻ የሚገለጽ ከጉድለት ሁሉ የጠራ ፍፁም የሆነ አምላክ ማለት ነው፡፡ በሁሉ ነገሩ እንከን አልባ የሆነ ጌታ ነው፡፡ ጥሩነት መገለጫው ነው፤ ቆንጆ እና ዉብ ነገር ሁሉ የሚገባው ለርሱ ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ከሰው ልጆችም ንፁህ እና ፅዱ ነገሮችን ብቻ ይቀበላል፡፡ የተበላሸና መጥፎ ነገርን አይቀበልም፡፡ በሌብነት፣ በማምታትም ሆነ በወንጀል የተገኘን ምንጩ ሐራም የሆነን ነገር አይቀበልም፡፡ ማንኛውም ሥራችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ለሱ ብቻ ታስቦ የተሠራ መሆን አለበት፡፡ የተፈቀደና መልካም ነገርም መሆን አለበት፡፡

አላህ (ሱ.ወ.) አማኞች ሁሉ ጥሩ ነገር እንዲበሉና ጥሩ ነገርም እንዲሠሩ አዟል፡፡ ይህም እስልምና በአካልም ሆነ በመንፈስ ንፅህና ጥራት ላይ ምን ያህል እንደሚያተኩር ያሳያል፡፡ ስለሆነም የዕለት ተዕለት ሥራችን፣ ዉሎአችን፣ ሶላታችን፣ ፆማችን፣ ዱዓኣችን ሁሉ ጥራት ያለው መሆን አለበት፡፡ ባጠቃላይ ለአላህ ብለን የምንሠራቸው የአምልኮ ተግባራት በሙሉ በጥራት የተሞሉ መሆን አለባቸው፡፡ በሱ ከማጋራት የፀዱ፣ ከፈጠራና አልባሌ ከሆኑ አመለካከቶች የጠሩ መሆን አለባቸው፡፡ አላህ ጥሩ ነገርን እንጂ አይቀበልምና፡፡

በተለይ በዚህ ሐላል ነገር ውድ በሆነበት ዘመን ስለ ዱዓችን ምላሽ ማጣት ስናስብ ስለ የሲሳያችን ምንጭ ሐላል ይሁን ሐራም ማጣራትና ራሣችንን መፈተሽ ይኖርብናል፡፡ የሰው ልጅ ልመናውና ተማፅኖው አላህ ዘንድ ተሰሚነት ይኖረው ዘንድ ለገቢ ምንጩ መጠንቀቅ አለበት፡፡ ዱዓእን ተቀባይነት ከሚያሳጡ ነገሮች መካከል የአንድ ሰው የሲሳይ ምንጩ ከሐራም ነገር መሆኑ ነው፡፡ አንድ ሰው ምግቡ፣ መጠጡም ሆነ የገቢ ምንጩ ሐራም ሆኖ ሳለ በጉስቅልና ዉስጥ ጭምር ሆኖ ጩኸቱን ወደ አላህ ቢያሰማ አላህ አይሰማውም፡፡ እናም በዚህ ዙሪያ በእጅጉ መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ ይህ ሐዲሥ ያሳስባል፡፡

www.alifradio.com

0 6574

 

عَنْ أَبىِ عَبْد الله النُّعْمَانِ بْنِ بَشير رَضىَ الله عَنْهُما قَالَ : سَمعْتُ رَسُولَ اُلله صَلَّى الله  عَلَيْه وآله وسَلَّمَ يَقُولُ ((إنَّ الْحلالَ بَيَّنٌ وإنَّ الْحَرَامَ بَيَّنٌ وبَيْنَحُما أُمُورٌ مُشْتَبِهَات لا يَعْلَمُهُنَّ كَثير منَ النَّاس, فَمَنِ اُتَقَى الشَّبُهَات فَقَد اُسْتَبْرَأ لدينه وعرْضه, ومَنْ وَقَعَ في الشُّبُهَات وَقَعَ في الْحَرَام كالرَّاعي يرْعَى حَوْلَ الحمَى يُوشكُ أَنْ  يَرْتَعَ فيه, أَلا وإنَّ لكُلَّ مَلك حَمى, أَلا وإنَّ حَمى اُلله مَحَارمُه, ألا وإنَّ في الْجَسَد مُضْغَةً إذَا صَلحَتْ صلحَ الْجَسَدُ  كُلهُ وإذَا فَسَدَ تْ فَسَد الْجَسَدُ كُلّهُ ألا وهيَ الْقَلْبُ)). رَوَاهُ الْبُخَارىُّ ومُسْلم.

 

አቢ ዐብደላህ ኑዕማን ኢብን በሺር እንደተላለፈው (ረ.ዐ.) የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለው ሲናገሩ ሰማሁ አሉ፡-

«ሐላል ነገር ግልፅ ነው፡፡  ሐራምም ነገር ግልፅ ነው፡፡ በሁለቱ መካከልም ብዙ ሰዎች የማያውቋቸው አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች አሉ፡፡ አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮችን የተጠነቀቀ እርሱ ከሃይማኖቱና ከክብሩ አኳያ ራሱን ያጠራ ነው፡፡ አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ላይ የወደቀ ሰው ግን እርሱ በሐራም ውስጥ ወደቀ፡፡ ምሳሌውም በጥብቅ ማሳ ዙሪያ (ከብቶቹን) እንዳሰማራ እረኛ ነው፤ ንቁ! ማንኛውም ንጉሥ ጥብቅ ክልል አለው፡፡ ንቁ! የአላህ ክልል እርሱ ሐራም ያደረጋቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ንቁ! በአካላችን ውስጥ አንዲት ቁራጭ ሥጋ አለች፤ እርሷ ከተስተካከለች መላው አካል የተስተካከለ ይሆናል፤ እርሷ ከተበላሸች ደግሞ መላው አካል  ይበላሻል፡፡ ንቁ! ይህች ቀራጭ ሥጋ ልብ ናት፡፡»

(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡)

መጠነኛ ማብራሪያ

ይህ ሐዲሥ መሠረታዊ በሐላልና ሐራም መርሆች ዙሪያ መሠረታዊ ከሆኑ ሐዲሦች መካከል አንዱ ነው፡፡ ሐዲሡ ከድንጋጌ አንፃር ሦስት ነገሮች መኖራቸውን ያመለክታል፡፡ እነርሱም ሐላል፣ ሐራም እና አጠራጣሪ ነገሮች ናቸው፡፡ ሐላል ነገሮች የሚባሉት የተፈቀዱ ነገሮች ናቸው፡፡ አንድ ነገር ሐራምነቱ እስካልተገለፀ ድረስ በመሠረቱ ሐላል አንደሆነ ነው የሚታወቀው፡፡ ሐራም ነገሮች ደግሞ ክልክል የሆኑ ነገሮች ናቸው፡፡ ሐራም መሆኑን እያወቀ ክልክል ነገር የፈፀመ ሰው ወንጀል ሰርቷል፣ የአላህን (ሱ.ወ.) ድንጋጌ ጥሷል፡፡  ስለዚህም ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ ሌላው አጠራጣሪ ነገር ሲሆን ሐላልም ሐራምም ሊሆን ይችላል፡፡ ሐላል ከሆነ መልካም፡፡ ሐራም ሊሆንም ስለሚችል ለስምና ክብርም ጥሩ ስላልሆነ ከመዳፈሩ ይልቅ መራቁ ይመረጣል፡፡

ሐላል ነገር ግልፅ ነው  ፡- አዎን ግልጽ ነው፡፡ ተደንግጓል፣ ይታወቃል፣ የተፈቀደ ነው፡፡ መልካም ነገር መብላት፣ መጠጣት፣ መልበስ፣ ማግባት፣ መነገድ …. እና ሌሎችም ሐላል የሆኑ እጅግ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ ከሐራም አንፃር ሲታይም ሐላል የሆነ ነገር ይበዛል፡፡

ሐራምም ግልጽ ነው፡፡ ይህ ነገር ሐራም ነው ተብሎ ተነግሯል፣ ተደንግጓል፣ ሁሉም ያውቀዋል፡፡ ነፍስ መግደል፣ ሌብነት፣ ዝሙት፣  አስካሪ መጠጥ መጠጣት… ሌላም ሌላም ሐራምነታቸው ግልፅ የወጣ ነገሮች አሉ፡፡

አጠራጣሪ ነገሮች – ሐላል ይሁን ሐራም በግልጽ አልተለየም፡፡ ተመሳስሏል፣ አሻሚ ነው፡፡ አንድም ግልፅ የሆነ ድንጋጌ ስላልተቀመጠለት፣ የተላለፈው መልዕክት ተመሳሳይ ትርጉም የያዘ በመሆኑ፣ ዕውቀቱና መረጃው ስለሌለ ወይም ደግሞ የሰው ልጅ ግንዛቤ ዉስን በመሆኑ ሊሆን ይችላል ያጠራጠረው፡፡

ሃይማኖቱንና ክብሩን ጠበቀ – አጠራጣሪ ነገሮችን ባለመሥራቱና በአጠራጣሪ ቦታዎች ላይ ባለመታየቱ ምክንያት ሃይማኖቱንም ስሙን ጠበቀ፡፡ ሐራም ነገር ቢሂን አስቀድሞ ተጠንቅቋልና ሰዎች ሃይማኖቱን በክፉ፣ ስሙንም በመጥፎ አያነሱትም፡፡

እንደ እረኛ – ጥብቅ በሆነ ማሳ አካባቢ ክብቶቹን የሚያግድ እረኛ እጅግ ካልተጠነቀቀ በስተቀር ከብቶቹ ወደሚያሳሳው አረንጓዴውና አጓጊው ማሳ ድንገት ዘው ብለው ሊገቡበት ይችላሉ፡፡ እንዲሁ ዉሎውን በአጠራጣሪ ነገሮች ዙሪያ ያደረገ ሰው በሂደት ወደዚያ ነገር መሳቡ አይቀርም፡፡ ስለዚህ ከወዲሁ መራቅ ይበጃል ነው መልዕክቱ፡፡ አጠራጣሪ ነገርን መተው ለልብ መረጋጋትን ይለግሳልና፡፡

 www.alifradio.com

0 673

ዕውቀት የመገብየትና ቁርኣን የማንበብ ትሩፋት

عَنْ عُقْبَةَ بْنِ عَامِرٍ، قَالَ:

خَرَجَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَنَحْنُ فِي الصُّفَّةِ، فَقَالَ:

((أَيُّكُمْ يُحِبُّ أَنْ يَغْدُوَ كُلَّ يَوْمٍ إِلَى بُطْحَانَ أَوْ إِلَى الْعَقِيقِ، فَيَأْتِيَ كُل يوم  بِنَاقَتَيْنِ كَوْمَاوَيْنِ زهراوين فيأخذهما فِي غَيْرِ إِثْمٍ، وَلَا قَطْعِ رَحِمٍ؟))

 

فَقُلْنَا: كلنا يَا رَسُولَ اللهِ! يحِبُّ ذَلِكَ!

قَالَ:

((أَفَلَا يَغْدُو أَحَدُكُمْ إِلَى الْمَسْجِدِ فَيَتعلَم، أَوْ يَقْرَأُ آيَتَيْنِ مِنْ كِتَابِ اللهِ عَزَّ وَجَلَّ؛ خَيْرٌ لَهُ مِنْ نَاقَتَيْنِ!

وَثَلَاثٌ؛ خَيْرٌ لَهُ مِنْ ثَلَاثٍ!

وَأَرْبَعٌ؛ خَيْرٌ لَهُ مِنْ أَرْبَعٍ!

وَمِنْ أَعْدَادِهِنَّ مِنَ الْإِبِلِ))!!

 

 

ዑቅባህ ኢብን ዓሚር (ረ.ዐ.) ባስተላለፉት ሐዲሥ እንዲህ አሉ ‹የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሰለም እኛ ወዳለንበት በረንዳ በመምጣት ‹በየዕለቱ ማለዳ ወደ ቡጥሐን ወይንም ወደ ዐቂቅ በመሔድ አንድም ወንጀል ሣይፈፅምና ዝምድናንም ሣይቆርጥ ሁለት ወፋፍራም ትላልቅ ሻኛ ያላቸው ግመሎችን ይዞ መምጣት የሚሻ ማነው?› አሉ፡፡ ሁላችንም ‹እንሻለን የአላህ መልእክተኛ ሆይ!›  አልናቸው፡፡  እርሳቸውም ‹እንግዲያውስ  ወደ መስጊድ ሒዱና ዕውቀት ገብዩ፤ ወይንም ከቁርኣን ሁለት አንቀፅ አንብቡ፡፡ ይህ ከሁለት ሴት ግመል ይሻላችኋል፡፡ ሦስት አንቀፅ ማንበብም ከሦስት ግመሎች የበለጠ ነው፡፡ አራት ማንበብም ከአራት ግመሎች የተሻለ ነው፡፡ ብዙ አንቀፆች መማር/ማንበብ ከብዙ ግመሎችም የተሻሉ ናቸው፡፡› በማለት ነገሩን። (ሙስሊም ዘግበውታል፡፡)

 

መጠነኛ ማብራሪያ

ቡጥሐንም ሆነ ዐቂቅ መዲና አቅራቢያ የሚገኝ የቦታ ሥም ነው፡፡ ግመል ደግሞ ዐረቦች ዘንድ እጅግ ዉድ እና ተፈላጊ እንሰሳ ነው፡፡ ሆኖም ግን ዕውቀት መገብየት እና ቁርኣንን የማንበብ ምንዳው ከየትኛውም ዓለማዊ ጥቅም የላቀ መሆኑን ለማሳየትና ሶሐቦቻቸውም ሆነ አማኞች ሁሉ ፊታቸውን ወደዚሁ በጎ ሥራ ያዞሩ ዘንድ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ይህንን ምሳሌ ለሰዎች በሚገባቸው መልኩ ተጠቅመዋል፡፡  ስለሆነም ይህንን ታላቅ ምንዳ እናገኝ ዘንድ በዕውቀት ፍለጋና የአላህን ቁርኣን በማንበብ መበርታት ይኖርብናል፡፡ የአላህን ቁርኣን መማር ትልቅ ክብር ነው፡፡ ምርጡ ሰውም ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረው ነው፡፡ አላህ ይወፍቀን፡፡

www.alifradio.com

0 523

በአላህ ነቢይ ላይ ሶላዋት ማውረድ እና ትሩፋቱ

አላህ (ሱ.ወ.) በመልዕክተኛው ላይ ሶለዋት እንድናወርድ አዞናል፡፡

{إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا} سورة الأحزاب (56)

‹አላህ እና መላእክቱ በነቢዩ ላይ እዝነት ያወርዳሉ፡፡ እናንተም ያመናችሁ ሆይ! በርሱ ላይ እዝነትን አውርዱ፡፡ ሰላምታንም ሰላም በሉ፡፡› (አል-አሕዛብ ፡ 56) በማለት፡፡

የአላህ መልዕክተኛም (ሰ.ዐ.ወ.) ሥማቸው የተወሳ እንደሆነ በርሣቸው ላይ ሶለዋት እንድናወርድ አዘውናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በርሣቸው ላይ ሶለዋት ማውረድ ያለውን ምንዳም አውስተውልናል፡፡

عن أبي هريرة  رضي الله عنه قال: قال النبي صلى الله عليه وسلمفإنه من صلى علي واحدة صلى الله عليه بها عشرا. )أخرجه مسلم وأبو داود والترمذي

ከአቢ ሁረይራ (ረ.ዐ.) እንደተላለፈው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ‹በኔ ላይ አንዲት ሰላት ያወረደ ሰው አላህ በሷ ምክኒያት አሥር ሰላቶችን በሱ ላይ ያወርድበታል፡፡›

ሶለዋት ማለት የአላህ እዝነት ማለት ነው፡፡ በነቢዩ ላይ ሶለዋት ስናወርድ አላህ (ሱ.ወ.) በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) እዝነቱን እንዲያወርድ እየለመንን ነው ማለት ነው፡፡

በአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ላይ ሶለዋት ለማውረድ (ለርሣቸው የአላህን እዝነት ለመለመን) በርካታ አባባሎች የመጡ ቢሆንም ዑለማኦች ይበልጥ የመረጡትና የተሟላው አባባል ይህ ነው፡፡

(: اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد)

‹አልላሁምመ ሶልሊ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ሙሐመዲን ከማ ሶለይተ ዐላ ኢብራሂመ ወዐላ ኣሊ ኢብራሂም ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ፡፡ አልላሁምመ ባሪክ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊ ሙሐመዲን ከማ ባረክተ ዐላ ኢብራሂመ ወዐላ ኣሊ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ› የሚለው ነው፡፡

ትርጉሙ – ‹ አላህ ሆይ! በኢብራሂም እና በቤተሰቦቹ ላይ እዝነትህን እንዳወረድክ ሁሉ በሙሐመድ እና በቤተሰቦቹ ላይ እዝነትን አውርድ፡፡ አንተ ምስጉን እና የተከበርክ ነህና፡፡ አላህ ሆይ! በኢብራሂም እና በቤተሰቦቹ ላይ በረከትህን እንዳወረድክ ሁሉ በሙሐመድ እና በቤተሰቦቹም ላይ በረከትህን አውርድ፡፡ አንደ ምስጉን እና የተከበርክ ነህና፡፡›

በአላህ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሶለዋት ማውረድ ትልቅ ምንዳ አለው፡፡ በርሣቸው ላይ ሶለዋት አለማውረድ ንፉግነት ነው፡፡ ኪሳራ ያስከትላል፡፡ በተለይ ሰብሰብ ብለው በተነሱ ሰዎች ላይ፡፡ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል-

 

وعن أبي هريرة – رضي الله عنه – قال : قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم – : ” ما جلس قوم مجلسـًا لم يذكروا الله ولم يصلوا على نبيهم – صلى الله عليه وسلم – إلا كان مجلسهم عليهم ترة يوم القيامة ، إن شاء عفا عنهم وإن شاء أخذهم “(رواه الترمذي (

ከአቢ ሁረይራ (ረ.ዐ.) እንደተወራው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል ‹የአላህን ሣያወሱና በነቢያቸዉም ላይ ሰለዋት ሣያወርዱ በአንድ ስብስብ የተቀመጡ ሰዎች ስብስባቸው የኪሣራ ነው፡፡ ከሻ ይምራቸዋል፣ ከሻም ይቀጣቸዋል፡፡› (ቲርሚዚ ዘግበውታል)

በሌላ ሐዲሥም

عن علي بن أبي طالب رضي الله عنه:  البخيل من ذكرت عنده ثم لم يصل عليرواه أحمد 

ከዐሊ ኢብኑ አቢ ጣሊብ (ረ.ዐ.) እንደተወራው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.)‹ንፉግ ማለት ሥሜ በርሱ ዘንድ ተወስቶ በኔ ላይ ሰለዋት ያላወረደ ሰው ነው፡፡› ብለዋል፡፡

ሶለዋት ዐለ ነቢ ዛሬ ላይ እየተረሱ ካሉ ተግባራት መካከል አንዱ ነው፡፡ ታላቁ ዓሊም ኢብኑ አልቀይም (አላህ ይዘንላቸው) ነቢዩ ላይ ሶለዋት ማውረድ ስላለው ምንዳ አርባ ትሩፋቶችን ዘርዝረዋል፡፡ ከነኚህም መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ

 1. የአላህ ትዕዛዝ የማክበር ተምሳሌት ነው፡፡ አላህ አዞበታልና፡፡
 2. አንድ ሶለዋት አሥር እዝነት ከአላህ እናገኛለን፡፡
 3. አሥር ደረጃ ከፍ ያደርጋል፣
 4. አሥር ምንዳ ያስገኛል፣
 5. ፃድቃን ከሆኑ የአላህ መላእክት ጋር መገጣጠም ነው፤ እነርሱም ሶለዋት ያወርዳሉና
 6. አሥር ወንጀል ያሳብሳል፣
 7. የአንድ ሰው ዱዓእ ምላሽ ያገኝ ዘንድ አንዱ ምክንያት ነው፣
 8. በቂያማ ቀን የነቢዩን ምልጃ ያስገኛል፣
 9. የመልዕክተኛውን (ሰ.ዐ.ወ.) ሐቅ የምንወጣበት አንዱ መንገድ ነው፣
 • አላህ ካሳሰበን ነገር ሁሉ ይጠብቀናል፣
 • ሶላዋት የሚያበዛ የትንሳኤ ቀን የነቢዩን ጉርብትና ያገኛል፣
 • አላህ እና መላእክትም እዝነታቸውን ያወርዱልናል፣
 1. ነፍሳችንን ያጠራልናል፣
 • የረሳነውን ነገር ያስታውሰናል፣
 • ለአንድ ስብስብ ማስዋቢያና ምንዳ ማግኛ ነው፣
 • አላህን የማስታወስ እና የማመስገን አካል ነው፣
 • የነቢዩ ዉዴታ መገለጫ ነው፣
 • የአላህ እዝነት ለማግኘት ሰበብ ነው፣
 1. በረከትን ያስገኛል፣
 • ለመስተካከልና ለመፅናት ያግዛል

.www.alifradio.com

 

 

0 320
Heart shape tree in lavender meadow for love symbol

ማግራራትና አለማካበድ

ዲናችን ገር ነው፡፡ ማክረር፣ ማጨናነቅ፣ ሰውን መፈናፈኛ ማሳጣት፣ የአላህ እዝነቱ ከቅጣቱ የሰፋ ከመሆኑ ጋር ሁሌም በቅጣቱና በቁጣው ማስፈራራት፣ ሐላሉ የበዛ ሆኖ ሳለ ሁሉን ነገር ሐራም ሐራም ማለት ሚዛናዊነትም ፍትሃዊነትም አይደለም፡፡ ሰዎች ከአላህ መንገድ እንዲርቁም አንዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡

ቡኻሪ አቢ ሁረይራን በመጥቀስ  ቡኻሪ ባወሩት ሐዲሥ የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-

عَنْ أَبِى هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنِ النَّبِىِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ፡
إِنَّ الدِّينَ يُسْرٌ ، وَلَنْ يُشَادَّ الدِّينَ أَحَدٌ إِلاَّ غَلَبَهُ ، فَسَدِّدُوا وَقَارِبُوا وَأَبْشِرُوا ، وَاسْتَعِينُوا بِالْغَدْوَةِ وَالرَّوْحَةِ وَشَىْءٍ مِنَ الدُّلْجَةِ ) رواه البخاري (39) ومسلم (2816(

‹ዲን ገር ነው፡፡ አንድም ሰው ዲንን አያከርርም ያሸነፈው ቢሆን እንጂ፡፡ አስተካክል፣ ቅረቡ፣ በርቱ፡፡ በጠዋት እና በማታ ታገዙ፡፡ ከሌሊትም የተወሰነውን በመውሰድ፡፡›

መጠነኛ ማብራሪያ-

ዲን ገር ነው – እስልምና የተወሳሰበ አይደለም፣ ለመረዳት አይከብድም፣ ጤናማ አዕምሮ ይቀበለዋል፣ የሚያዝባቸው ነገሮችም ገር እና መልካም ናቸው፡፡ ለዚህም ሆነ ለመጭው ዓለም የሚጠቅሙ ናቸው፡፡ ፋይዳቸውም ለራስ ነው፡፡

ዲኑ ያሸነፈው ቢሆን እንጂ – የተሠጠንን በልክ መያዝ አለብን፣ ከአቅሙ በላይ የተሸከመ ሰው ይደክማል፣ ይወድቃል፣ ይሰበራል፡፡ የማይችሉትን ብዙውን ከማግበስበስ የሚችሉትን በጥቂቱ ይዞ መጓዝ፡፡

ፈሰዲዱ /አስተካክሉ –  ትክክለኛውን መንገድ ያዙ፣ አሳምሩ፣ አስተካክሉ፡፡ በሥራ፣ በንግግር፣ ትክክለኛ ሁኑ፡፡ ችላ ሳትሉ ድንበርም ሳታልፉ የቻላችሁትን ያህል አላህን ፍሩ፡፡

ወቃሪቡ /ቅረቡ – ባትችሉ እንኳን አትስነፉ፣ ሞክሩ፣ ወደሚፈለገው ነገር ተጠጉ፣ ጣሩ፣ የቻላችሁትን ያህል ቅረቡ፡፡ አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትምና፡፡

ወአብሽሩ /በርቱ – ምንዳ ይጠብቃችኋልና አይዟችሁ፣ በርቱ፣ ጠንክሩ፣ አትፍሩ፣ ተስፋ አድርጉ፣ በጎ ጠርጥሩ፡፡ ሥራችን አነሰ ብላችሁ አትስጉ፡፡ ሥራችሁ ትንሽ ቢሆንም ዘውትሩበት፡፡ መካከለኛና ሚዛናዊ ሁኑ፡፡

በጠዋት፣ በማታና ከሌሊትም በተወሰነው ታገዙ – ወሳኝ ጊዜያት ናቸውና፡፡ በነኚህ ጊዜያት ዉስጥ የሰው ልጅ ነፍስ ጥሩ ስሜት ይኖራታል፣ የተነቃቃች ናት፡፡ መንገደኛ ጉዞ ለማድረግ ጥሩ የሚባሉ ሰዓታት ናቸው፡፡ ለመጓጓዣ እንሰሳም ሆነ ለተጓዥ መልካም ናቸው፡፡ አያደክሙም፡፡ እነኚህን ጊዜያት ተጠቀሙባቸው፡፡ አላህን በጥሩ ስሜት አምልኩት፡፡ በርትታችሁ ሰንቁ፡፡ ጥሩ ስሜትና ተስፋ ላይ ሆናችሁ ወደ አላህ ተጓዙ፡፡

ይህ ሁሉ አላህ ለባሮቹ ያለው እዝነት ነው፡፡ አግራሩ አታካብዱ አታጨናንቁ አታስፈራሩ ያቻልነውን ያህል አላህን እናምልከው ተዉን

 

0 483

እሳተ ጎሞራ
ከመሬት ገጽታ በታች ያለ የማግማ ክምችት ፈንድቶ ወደ ውጭ በተራራ ላይ የቀለጠ አለት ( ላቫ) ሲፈስ ይፈጠራል። እሳተ ጎሞራዎች ለመፈንዳት ከባድ እፈና (ጫና) እና ማግማ አንድ ላይ መገኘት አለባቸው። አፈናው ተራራው እንዲፈነዳ ሲያደርግ፣ ማግማው ደግሞ ከተራራው ውስጥ አመድ፣ ድኝ፣ የውሃ እንፋሎት፣ እና ሌሎች ጋዞችና ብጥስጣሽ ዓለቶች እንዲፈናጠሩ ያደርጋል።

0 477

ሙስሊሞች ለዓለም ስልጣኔ ምን አበረከቱ?

3. የሰውልጅ – የአምላክን ጸጋዎች ተጠቃሚ
በስነ-ፍጥረት ውስጥ የሚገኙት ሁሉም ህያው ፍጥረታት በፈጣሪ የፀጋ ጎጆ ውስጥ ይኖራሉ። ሆኖም ግን ዋና የነዚህ ፀጋዎች ተጠቃሚ የሰው ልጅ ነው። የሰው ልጅ ፍጥረት ምን ይመስላል? እሱ ወይም እሷ ለምን እዚህ ምድር ለይ ይኖራሉ? እነዚህ ጥያቄዎች በብዙ ሰዎች ጭንቅላት ውስጥ የሚመላለሱ ሲሆን፤ ኢስላም ለነዚህ ጥያቄዎች ያለውን ምላሽ ከዚህ በታች ለመዳሰስ ተሞክሯል።
የሰው ልጅ ተፈጥሮ
ذَٰلِكَ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ الْعَزِيزُ الرَّحِيمُ ﴿٦﴾ الَّذِي أَحْسَنَ كُلَّ شَيْءٍ خَلَقَهُ وَبَدَأَ خَلْقَ الْإِنسَانِ مِن طِينٍ ﴿٧﴾ ثُمَّ جَعَلَ نَسْلَهُ مِن سُلَالَةٍ مِّن مَّاءٍ مَّهِينٍ ﴿٨﴾ ثُمَّ سَوَّاهُ وَنَفَخَ فِيهِ مِن رُّوحِهِ وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُونَ ﴿٩﴾
“ይህ የሩቁንም የቅርቡንም ዐዋቂ ሃያልም፣ አዛኝም የሆነው (አምላክ) ነው። ያ ሁሉንም ነገር አሳምሮ የፈጠረው -የሰውን ልጅ የአፈጣጠር ሂደትም ከጭቃ የወጠነ (አምላክ) ነው። ከዚያም ዘሮችን ከጠለለ ደካማ ፈሳሽ አደረገ (ፈጠረ)። ከዚያም አስተካከለው። ከመንፈሱም ነፋበት። ለናንተም መስሚያ (ጆሮን)-መመልከቻ (ዓይንን)-ልቦናንም አደረገላችሁ። ግና ምስጋናችሁ እጅግ አናሳ ነው።” (አል-ሰጃዳህ 32፤6-9)
ከዚህ የቁርኣን አንቀጽ የሰው ልጅ ተፈጥሮ አካላዊ፣ አእምሮአዊና መንፈሳዊ መሆኑ ተገልጿል። ‘ጭቃ’ የሚለው ቃል በሰው ልጅ ተፈጥሮ ግብዓት አካላዊ ስጋ የሚለውን ይወክላል። ይህ ስጋዊ ግብአት መኖሩ የሰው ልጅ የራሱን አምሳያ በመተካት የሕይወትን ቀጣይነት እንዲያረጋግጥ ይገፋፋል ያስገድዳል።
በሌላ በኩል ደግሞ የሰው ልጅ የማሰብና የማገናዘብ ችሎታም ተሰጥቶታል። ነገር ግን ማገናዘብ ብቻ የተፈጥሮን ምስጢር በሙሉ ለማወቅ በቂ አለመሆኑ ግልጽ ነው። ማገናዘብ አንድን እምነት ወይም አስተሳሰብን ለማጠናከር አይጠቅምም ማለት ግን አይደለም። የሃይማኖት ተቃራኒም አይደለም። በእርግጥም የማሰብና የማገናዘብ ችሎታን መጠቀም ተቀባይነት ብቻ ያለው ሳይሆን ትዕዛዝም ነው። ቅዱስ ቁርኣን እንዳስቀመጠው።
أَوَلَمْ يَتَفَكَّرُوا فِي أَنفُسِهِم مَّا خَلَقَ اللَّهُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا إِلَّا بِالْحَقِّ وَأَجَلٍ مُّسَمًّى وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ النَّاسِ بِلِقَاءِ رَبِّهِمْ لَكَافِرُونَ [٣٠:٨]
“የራሳቸውን(አፈጣ’ጠር) አያስተውሉምን? አላህ ሰማያትንና ምድርን- በመካከላቸው ያሉ ፍጡራንንም በእውነትና ለተወሰነ ጊዜ እንጅ አልፈጠረም። ግና ከሰዎች ብዙዎቹ ከጌታቸው ጋር መገናኘታቸውን ያስተባብላሉ።” (አር-ሩም 30፤8)
أَوَلَمْ يَنظُرُوا فِي مَلَكُوتِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا خَلَقَ اللَّهُ مِن شَيْءٍ وَأَنْ عَسَىٰ أَن يَكُونَ قَدِ اقْتَرَبَ أَجَلُهُمْ فَبِأَيِّ حَدِيثٍ بَعْدَهُ يُؤْمِنُونَ [٧:١٨٥]
“የሰማያትንና የምድርን ግዛቶች-አላህ የፈጠራቸውንም ሌሎች ፍጡራን አያስተውሉምን? ምናልባትም የሞት ጊዜያቸው ቅርብ ሊሆን አይችልምን? (ታዲያ ምን አዘናጋቸው)? ከርሱ (ከቁርኣን) ሌላ የየትኛውን መልዕክት ሊያምኑ (እና ሊቀበሉ) ነው።” (አል-አዕራፍ ፤ 185)
በሰው ልጅ አካላዊ ተፈጥሮ ውስጥ የሚገኙትን ሌሎችም ፍጥረታት ይጋሩታል። የማሰብ ደረጃው ይለያይ እንጂ እንስሳቶችም የማሰብ ችሎታ አላቸው። ነገርግን አሁንም ቢሆን ቁርኣን እንደሚገልጸው በሰው ልጅ ብቻ አላህ ከሱ ከሆነ መንፈስ ነፋበት። ይህ መንፈስ ነው የሰው ልጅን መንፈሳዊና ሞራላዊ ባህሪዎችን ያጎናጸፈው። በተጨማሪም የሰው ልጅ በፍጥረታት የተለየ ቦታ እንዲኖረውና ቁንጮ እንዲሆን አስችሎታል።
وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ وَحَمَلْنَاهُمْ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا [١٧:٧٠]
“የአደም ልጆችን (ከሌሎች ፍጡራን) አላቅናቸው። በየብስም በባሕርም አሳፈርናቸው። ከመልካም ሲሳይም ለገስናቸው። ከፈጠርናቸው ፍጡራን ከብዙዎቹ አላቅናቸው።” (አል-ኢስራእ 17፤70)
አላህ (ሱ.ወ) መልአክትን ለሰው ልጆች አባት አደም ስገዱ ብሎ ማዘዙ ለዚህ ታላቅ ክብር መጎናጸፉ ማሳያ ነው።
وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ أَفَتَتَّخِذُونَهُ وَذُرِّيَّتَهُ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِي وَهُمْ لَكُمْ عَدُوٌّ بِئْسَ لِلظَّالِمِينَ بَدَلًا [١٨:٥٠]
“ለመላዕክት-ለአደም ስገዱ ባልን ጊዜ (የሆነውንም አስታውስ)። (ሁሉም) ሰገዱ፤ ዲያብሎስ ሲቀር። እርሱ ከአጋንንት ነበር። በጌታው ትዕዛዝ አመጸ። እርሱንና ዝርያዎቹን፤ (በግልፅ) ጠላቶቻችሁ ሆነው እያሉ፤ ከኔ ሌላ አጋር አድርጋችሁ ትይዟቸዋላችሁን? ለበዳዮች የሚሰጠው ልዋጭ የከፋ ነው!” (አል-ከህፍ 18፤50)
አይህ የክብር ዙፋን የሰው ልጅ በምድር ላይ ተተኪ ሆኖ ጌታውን ከማገልገል ጋር የተቆራኘ ነው። ይህ የምትክነት ሚና ከባድ ኃላፊነት እንደመሆኑ ትክክለኛውን ምርጫ መውሰድን ይጠይቃል። የእንደዚህ ዓይነት ምርጫ አለማድረግ ያን የክብርና ልዩ ቦታ ወደ ማጣት ያመራል። የሰው ልጅ ከዚህም አንሶ ከእንስሳ በታች ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ሊፈጠርም ይችላል። እንዲ ከሆኑት መካከል።
وَلَقَدْ ذَرَأْنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرًا مِّنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا أُولَٰئِكَ كَالْأَنْعَامِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ أُولَٰئِكَ هُمُ الْغَافِلُونَ [٧:١٧٩]
“የማይገነዘቡባቸው ልቦች፤ የማያዩባቸው ዓይኖች፤ የማይሰሙባቸው ጆሮዎች ያሏቸውን በርካታ ሰዎችና አጋንንት ለገሃነም ፈጠርን። እነርሱ ልባቸው እንደእንስሳ፤ ከዚያም የባሱ ናቸው። እነርሱ በእርግጥም (ማስጠንቀቂያውን) የዘነጉ ናቸው።” (አል-አዕራፍ 7፤179)
አካላዊ፣ አእምሮአዊና መንፈሳዊ የሰው ልጅ ግብዓቶች ተነጣጥለው እንደ ሶስት የተለያዩ ክፍሎች የሚታዩ አይደሉም። የማይስማሙ ነገሮችም አይደሉም። የሰው ልጅ ከላይ የወረደ መላዕክም፤ ከእንስሳት በዝግመታዊ ለውጥ የመጣ ፍጡርም አይደለም። ነገር ግን የሰው ልጅ ኃላፊነት የሚሰማው ብሎም ከመላዕክት ወደበለጠ ደረጃ የሚቀመጥ ወይንም በተቃራኒው ከእንስሳት አንሶ ወደ ታች ሊዘቅጥ የሚችልበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል።
“የተከለከለችው ዛፍ” የሰው ልጅን የስነ-ምግባር ሁኔታ በሙሉ ትወክላለች። ይህች ክስተት ነፃ ምርጫን፣ መጓጓትን፣ ውሳኔ መውሰድን፣ መሳሳትን፣ ስህተትን መረዳት፣ መማፀንና ምህረትን መሻትን ቁልጭ አድርጋ ታሳያለች። የሰው ልጅ ያጋጠመውን ስነምግባራዊ ፈተናዎች ትወክላለች። ከነዚህም ውስጥ
1. ፍፁም ስጋዊ/አካላዊ ከሆነው አስተሳሰብ በማለፍ በስጋዊ ስሜት ከመተዳደር ይልቅ ድንበር አልፎ መሻገር። በስሜትና በሥጋ ከመመራት መቆጠብ።
2. መንፈሳዊና አእምሮን ተጠቅሞ ነገሮችን ምክንያታዊ የማድረግ ልምድን ማዳበር ከዚያም ለአምላካችን አላህ (ሡ.ወ) በሚል ሙሉ ቆራጥነትና መስዋእት በመክፈል ከሱ ትዕዛዛት ጋር ማቆራኘት፤ ማዋሃድ።
3. አላህን በመታዘዝና በማመጽ የሚከሰቱትን ውጤቶች መገንዘብ።
4. ምድራዊ ፈተናን ለማለፍ መታገል ደግሞ ከሞት በኋላ ያለውን ጀነትን ለመግባት ብቻ ሳይሆን ለአላህ (ሡ.ወ) ቅርብ በመሆን የሚገኘውን በረከት ለመጎናጸፍም ጭምር መሆን ይገባዋል።
የመፈጠር ዓላማ
ቁርኣን የሰው ልጅን የመፈጠር ዓላማ በሚከተለው የቁርኣን ጥቅስ ጠቅለል ያደርገዋል።
وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ [٥١:٥٦]
“አጋንንትንም ሰዎችንም ሊያመልኩኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም።’’ (አዝ-ዛሪያት 51፤56)
አላህን ማምለክ ማለት ከላይ የሚታየውን ቃላዊ ትርጉም ብቻ ማለት አይደለም። ስርዐተ-ፀሎት ወይም ሌሎች መስዋእት የሚጠይቁ ክንውኖች በመፈጸም ብቻም የተገደበ አይደለም። ስርዓተ- ጸሎት፣ መስዋእት የሚጠይቁ ክንውኖች በርግጥ የራሳቸው የሆነ ቦታና ደረጃ አላቸው። አሁንም ቢሆን “ማምለክ” በኢስላም ከመደበኛ ትርጉሙ በዘለለ ጠቅለል ያለ (comprehensive) መልዕክትን ይይዛል።
ማንኛውም ተግባር የአምልኮት ክንውን ነው፤ ሁለት መሰረታዊ መስፈርቶችን እስካሟላ ድረስ። በመጀመሪያ ሆን ተብሎና ታቅዶበት (ኒያ ተስተካክሎ) የተፈጸመ መሆን አለበት። በሁለተኛ ደረጃ አላህ ባስቀመጣቸው ገደቦች ስር መሆን ይኖርበታል። ስለዚህም ማንኛውም ልማዳዊና አካላዊ እንቅስቃሴዎች፦ መብላት፣ መጠጣት፣ መተኛት እንዲሁም ‘ሐጢያት’ ያልሆኑ መዝናናቶችና የመሳሰሉ ነገሮችም ከላይ የተቀመጡትን መስፈርቶችን እስካሟሉ ድረስ አምልኳዊ ተግባራት ሊሆኑ ይችላሉ።
ስለዚህም “ማምለክ” ሰፊ ትርጉም ስለሚይዝ የሰው ልጅ የተለያዩ የሕይወት መስኮችን ፈጠራዊ በሆነ መልኩ መከፋፈል በኢስላም ውድቅ ነው። ተቀባይነትም የለውም። በጥቅሉ በኢስላም እይታ ሕይወት እርስ በእርሱ የተቆራኘና የተሳሰረ ነው። በውስጡም ግብረገብነት፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቀሴዎችን በተናጠልም ሆነ በህብረት የሚሰሩ ነገሮችን ያካትታል። በእርግጥም የሰው ልጅ ከሚገጥሙት ፈተናዎች አንዱ እነዚህን እንቅስቃሴዎች ከአምላካዊ መመሪያዎች ጋር ማገናኘትና ማዋሃድ ነው። ያ ፈተና ነው፤ የሰው ዘርን በምድረ ላይ የአላህ ኸሊፋ (ምትክ አስተዳዳሪ) ሆኖ እንዲሾም ያስቻለው። አላህም ምድራዊ ሕይወትን ፈተና አድርጓታል።
الَّذِي خَلَقَ الْمَوْتَ وَالْحَيَاةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا وَهُوَ الْعَزِيزُ الْغَفُورُ [٦٧:٢]
“ማንኛችሁ ሥራው መልካም እንደሆነ ሊፈትናችሁ-ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ (አምላክ) ነው። እርሱም አሸናፊው-መሓሪው ነው።” (አል-ሙልክ 67፤2)
አንድም የሰው ልጅን ተፈጥሮ እንዲሁም የመፈጠሩ ዓላማን ማወቅና መቀበል ብሎም ኸሊፋ የመሆን ሚና፤ በተጨማሪም አንድ ሰው ከተፈጥሮአዊና ከማህበራዊ ስርዓቶች ጋር ሊኖር የሚገባውን ግንኙነትና ትስስር ይወስነዋል።

ethiomuslim

0 626

የመድኃኒት አለርጂ ምን ማለት ነው?

የመድኃኒት አለርጂ መድኃኒት ከመጠቀም ጋር ተያይዞ የሚመጣ ያልተለመደና ያልተፈለገ የጐንዮሽ ጉዳት ነው፡
የተለያዩ ዓይነት የመድኃኒት አለርጂዎች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ይህም ከቀላል የቆዳ ላይ ሽፍታ እስከተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን የሚያጠቃ ከባድ አለርጂ ሊሆን ይችላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች ይልቅ አለርጂ በቆዳ ላይ ይታያል፡፡ የመድኃኒት አለርጂ ምልክቶችን ማወቅ በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ ነው፡፡ ምክንያቱም ሕይወትን አደጋ ላይ ሊጥሉ ስለሚችሉ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የመድኃኒት አለርጂ የሚከሰተው መድኃኒትን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲወስዱ ላይሆን ይችላል፡፡ መድኃኒቶች ከአንድ ጊዜ (ከአንድ ዶዝ ለምሳሌ ከአንድ እንክብል) በላይ ሲወሰዱ የሚያጋጥም ነገር ነው፡፡ ይህንን ስንል ግን በመድኃኒት ምክንያት የሚመጡ ጐጂ ባህሪያት ወይም የጐንዮሽ ጉዳቶች ሁሉ አለርጂ ማለት እንዳልሆኑ መጠንቀቅ ይገባል፡፡ ከሚያጋጥሙ የጐንዮሽ ጉዳቶች ውስጥ አለርጂ የሚሆኑት አብዛኛውን ጊዜ ከ10 በመቶ ያነሱ ናቸው፡፡
የመድኃኒት አለርጂ መንስኤዎች
የመድኃኒት አለርጂ የሚከሰተው የምንወስደውን መድኃኒት ሰውነታችን እንደ ባዕድ ነገር ቆጥሮ ለመከላከል በሚያደርገው ጥረት ነው፡፡
 በተደጋጋሚ አንድን መድኃኒት መጠቀም፣ መድኃኒቱን ከፍ ባለ መጠን መጠቀም፣ በአፍ ከመውሰድ ይልቅ መድኃኒት በክትባት መልክ መውሰድ፣ በቤተሰብ ውስጥ አለርጂ የገጠመው ሰው መኖር፣ ለተለያዩ ምግቦች /እንቁላል፣ ዓሣ/ አለርጂ መሆን በመድኃኒት ምክንያት ለሚመጣ አለርጂ ተጋላጭነት እንዲጨምር ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የመድኃኒት አለርጂ እንዲከሰት ከሚያደርጉ መድኃኒቶች ውስጥ ለመጥቀስ ያህል የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች /አስፕሪን፣ አይቡፕሮፌን/፣ የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች/ፔኒሲሊን፣ ቴትራሳይክሊን/ ወዘተ ይገኙበታል፡፡
የመድኃኒት አለርጂ ምልክቶች
የመድኃኒት አለርጂ ሲፈጠር የተለያዩ ዓይነት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፡፡ እነዚህ የአለርጂ ምልክቶች እንደ መድኃኒቱ ዓይነት እና ለመድኃኒቱ የመጋለጥ መጠን ሊለያዩ ይችላሉ፡፡ የተለመዱት የመድኃኒት አለርጂ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
– የቆዳ ሽፍታ
– ትኩሳት
– የጡንቻና የመገጣጠሚያ አካባቢዎች ህመም
– የብሽሽት እብጠት (Lymph Node Swelling)
ከመድኃኒት ውጪ ያሉ አለርጂዎች አለርጂ ለሚሆነው ነገር በተጋለጥን በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚከሰቱ ሲሆን የመድኃኒት አለርጂ ግን ብዙውን ጊዜ መድኃኒቱ ከተወሰደ ከቀናት ወይም ሳምንታት በኋላ ይታያሉ፡፡ ሌላው የመድኃኒት አለርጂ ዓይነት ሕይወትን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችልና በጤና ተቋም ደረጃ በአፋጣኝና በድንገተኛነት መፍትሔ ሊሰጠው የሚገባ አናፊላክሲስ ወይም አናፊለክቲክ ሪአክሽን የሚባለው ዓይነት ነው፡፡
የዚህ ዓይነቱ አደገኛ አለርጂ መገለጫዎች በቆዳ ላይ የማሳከክ ስሜት፣ መቅላት፣ የትንፋሽ ማጠር፣ ራስን መሳት፣ ፈጣን ወይም የተዛባ የልብ ምት፣ የፊት፣ የከንፈር፣ የምላስ፣ እጅ፣ እግር ወይም የመገጣጠሚያዎች እብጠት ሲሆኑ የዚህ ዓይነቱ አለርጂ መድኃኒቱ በተወሰደ በአራት ሰዓታት ውስጥ ሊታይ ይችላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ግን በሰከንዶች ወይም በደቂቃዎች ውስጥ ይከሰታል፡፡
የጤና ባለሙያ ዕርዳታ የሚያስፈልግዎ መቼ ነው?
የሚወስዱት መድኃኒት ምልክቶቹ ቀለል ያሉ ከሆኑ ወደ ሌላ መድኃኒት ሊቀየርሎት፣ መድኃኒቱን እንዲያቋርጡ ሊደረግ ወይንም ምልክቶቹን የሚያጠፋ መድኃኒቶች ሊታዘዝሎት ይችላል፡፡ በተለይ እንደ ትኩሳት፣ ማስመለስ የመሳሰሉት ምልክቶች ከታየብዎት ወዲያውኑ ወደ ጤና ተቋም መሄድ ይገባዎታል፡፡
ምርመራዎች
ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ የመድኃኒት አለርጂ ሊታወቅ /ሊለይ/ የሚችለው ታማሚው ላይ በሚታዩት ምልክቶች ሲሆን የጤና ባለሙያዎች እነዚህን ምልክቶች በሥልጠና ያውቋቸዋል፡፡ አልፎ አልፎ የደም ምርመራ እና ሌሎችም ምርመራዎች ሊያስፈልጉ ይችላሉ፡፡
የመድኃኒት አለርጂ ሕክምና
ከጤና ባለሙያ በሚገኝ ምክር አንዳንድ ቀለል ያሉ የአለርጂ ምልክቶች በቤት ውስጥ ሊታከሙ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፡- በቆዳ ላይ ለሚወጣ ሽፍታ በቀዝቃዛ ውኃ ገላን መታጠብና ቀለል ያሉ ልብሶችን መልበስ ይጠቅማል፡፡ የማሳከክ ስሜትን ለመቀነስ ደግሞ የጤና ባለሙያን አማክሮ መድኃኒቶችን መውሰድ ይቻላል፡፡ ከበድ ላሉ የመድኃኒት አለርጂ ምልክቶች /ለምሳሌ፡- አናፊላክሲስ/ በሚከሰቱበት ጊዜ ግን ወዲያውኑ ወደ ጤና ተቋም መሔድ ይገባል፡፡
የመድኃኒት አለርጂን በመድኃኒት ማከም ካስፈለገ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች አስቀምጦ መመልከት ይቻላል
1. ቀለል ያሉ የመድኃኒት አለርጂ ምልክቶች /አልፎ አልፎ የቆዳ ላይ ማሳከክና ሽፍታ/ ዓላማው በመድኃኒቱ ምክንያት የታየውን ችግር እና አለርጂ ማስቆም ሲሆን Antihistamine /አንቲሂስታሚን/ በተባሉት የመድኃኒት ክፍል ሥር የሚገኙ መድኃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡ ብዙውን ጊዜም አለርጂ ያስከተለው መድኃኒት እንዲቋረጥና በምትኩ ሌላ እንዲታዘዝ ይደረጋል፡፡
2. ጠንከር ያሉ የመድኃኒት አለርጂ ምልክቶች /የሰውነት ሙሉ በሙሉ ሽፍታ እና ማሳከክ/ እና ሕይወትን አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ከባድ የመድኃኒት አለርጂ ምልክቶች /የትንፋሽ ማጠር፣ ራስን መሳት/ በዚህ ጊዜ አለርጂውን ያስከተለው መድኃኒት ወዲያውኑ እንዲቆም የሚደረግ ሲሆን የተፈጠሩትን አካላዊ ችግሮች የሚያሽሉ መድኃኒቶች ለታማሚው ይሰጣሉ፡፡ አለርጂው በጣም ከባድ ከሆነ ጤና ተቋም ውስጥ ተኝቶ መታከም የግድ ሊሆን ይችላል፡፡
የመድኃኒት አለርጂን እንዴት መከላከል ይቻላል?
የመድኃኒት አለርጂን ለማስቀረት የሚያስችል መንገድ ባይኖርም እንኳን ለመድኃኒት አለርጂ የመጋለጥ መጠንን መቀነስ ይቻላል፡፡ ማንኛውም መድኃኒትን የሚወስድ ግለሰብ ታዘለት የሚወስደውን መድኃኒት ምንነትና የጎንዮሽ ጉዳቶቹ ምን ምን እንደሆኑ ከጤና ባለሙያ ጠይቆ መረዳት ይገባዋል፡፡ በመድኃኒቱ ምክንያት የአለርጂ ምልክቶች ያጋጠመው እንደሆን መድኃኒቱን በራሱ ከማቋረጥ ይልቅ ወደ ጤና ተቋም መሔድ ይኖርበታል፡፡
ቀደም ሲል የወሰዱት መድኃኒት የአለርጂ ምልክት አምጥቶብዎት ከነበር በድጋሚ መድኃኒቱን መውሰድ ስለሌለብዎት መድኃኒቱ ደግሞ እንዳይታዘዝልዎት ለጤና ባለሙያዎ ያሳውቁ፡፡
ለአንድ ታካሚ ታዞ የነበረ መድኃኒት አለርጂ ቢያስከትልበትና በሌላ ጊዜ ከሌላ የጤና ተቋም ቢሔድ መድኃኒቱ መልሶ እንዳይታዘዝለት ለማድረግ የአለርጂ መታወቂያ ካርድ በአገር ደረጃ ተዘጋጅቶ በየጤና ተቋማቱ ይገኛል፡፡ የዚህ መታወቂያ ካርድ ዋና ዓላማ ማንኛውም አለርጂ የገጠመው ታካሚ አለርጂ ያስከተለበትን መድኃኒት ስም በመታወቂያ ካርዱ ላይ በጤና ባለሙያ እንዲጻፍለት በማድረግ ለግሉ እንዲይዝ እና በማንኛውም በሚሔድበት የጤና ተቋም መድኃኒት ሳይታዘዝለት በፊት ካርዱን ለጤና ባለሙያው በማሳየት በድጋሚ በአለርጂው እንዳይጠቃ መካላከል ይቻላል፡፡

ምንጭ:የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን)

0 654

ስነ-ውልደት(Part-2)
የፅንስ ወንድ ወይም ሴት መሆን
——————————-
ለሽል ፆታ ዋናውን ሚና የሚጫወተው የወንድ የዘር ፈሳሽ እንጂ የሴት እንቁላል አይደለም፡፡ የሚወለደው ህፃን ፆታ ማለትም ሴት ይሁን ወንድ የሚመሰረተው ባለ ሃያ ሶስት ጥንድ /Chromosomes/ ከሆኑ የእናትና ባህሪ ከሚይዘው እንቁላልና ባለሃያ ሶስት ጥንድ /Chromosomes/ የአባትን ባህሪ ከሚይዘው የወንድ ዘር ሆኖ የሴቷ xx በሚል ሲገልፅ የወንዱ በ xy ይገለፃል፡፡
በመጀመሪያው ደረጃ ፆታን የሚለየው ልክ እንደተፀነስ ሲሆን የሴቷን እንቁላል ከሚያስፀንሰው በወንዴው የዘር ፈሳሽ ውስጥ ባለው ክሮሞዛም /Chromosomes/ በሚባል Chemical ይወሰናል፡፡ ከላይ እንደተገለፀው የወንዴው በ xy ሲሆን የሴቷ ከ xx ተብሎ ሲገለጽ በሚችል ነው ዘር የተሰራው፡፡ የወንዴው ዘርና የሴቷ ዘር ሲገናኙ በመጀመሪያ ደረጃ ህዋሶቹ ይለያያዩ የወንዴዉ የነበረው xy የነበረው x እና y ይሆናል የሴት ደግሞ xx የነበረው x ና x ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት ፅንስ የሚፈጠረው x ከሚባለው የወንዴ ዘር ከሆነ ከሴቷ x ብቻ ስለሚመጣ xx ይሆናል ይህ ማለት ሴት ነው ማለት ነው ሆኖም ከወንዴው y ከመጣ xy ይሆንና ወንድ ይሆናል ማለት ነው፡፡
‹‹ወንድና ሴትን በጥንድ ፈጠረ ከሚፈናጠር ከሆነው የፈሳሽ ጠብታ›› ሱረቱ አል-ነጅም 53፡ 45 – 46)
ከዚህ በፊት እንዳየነው /ኑጥፋህ/ ማለት ጠብታ ሲሆን /ቱምና/ የሚለው የአረብኛ ቃል ትርጉሙ የሚፈናጠር፣ የሚረጭ፣ የሚለጠፍ ይሆናል፡፡ የሚፈናጠርዋ የሚራጭ፣ የሚለጠፍ ደግሞ የወንድ ዘር ነው፡፡ ስለዚህ ከሴቷ እንቁላል ለየት አድርጐ የሰው ልጅ ወንድም ይሁን ሴቱን ከወንድ ዘር እንደተፈጠረ ይገልፃል፡፡ ይህ ከላይ እንደገለፅኩት ለፆታ ወሰኙ የወንድ ዘር እንደሆነ ያስገነዝበናል፡፡
ቁርአን በሌላ አንቀፅም እንዲህ ይላል፡-
‹‹(የሰው ልጅ) የሚረጭ፣ የሚፈናጠር ጠብታ አልነበረምን ከዚያ የረጋ ደም አልሆነም እናም (አላህ) በሚያምር ሁኔታ (እንዲህ በዚህ መልኩ) ፈጠረው ከሱም ጥንድ ሲሆኑ ወንድና ሴትን አደረገ›› (ሱረቱ አል-ቂያማ 75፡37 – 39)
እዚህም ጋር ጥቂቷን ጠብታ በመግለፅ ለፅንስ ፆታ ወሳኙን ቦታ የሚይዘው የወንድ የዘር ፈሳሽ እንደሆነ ይገልፃል፡፡
በተለምዶ በህንደ አገር ውስጥ አማት የልጅ ልጇ ወንድ እንዲሆንላት ጥልቅ የሆነ ፍለጐት አላት እናም የተወለደው ልጅ የምትፈለገውን አይነት ፆታ ከሌለው ምክንያቷ ምራቷ /የልጇ ሚስት/ ነች በማለት ትወቅሳለች፡፡ የሚወለደው ፆታን በተመለከተ ወሳኙ የወንድ የዘር ፈሳሽ እንጂ የሴት እንቁላል አለመሆኑን ቢያውቁና መውቀስ አለብን ብለው የሚያምኑ ከሆነ ምራታቸውን ሳይሆን እራሱ ልጃቸውን ተጠያቂ ማድረግ ነበረባቸው ምክንያቱም በቁርአንም ይሁን በሳይንስ ለሚወለደው ህፃን ፆታ ወሳኙ የወንድ የዘር ፈሳሽ እንጂ የሴቷ አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ አንድ ሙስሉም የወንድ የዘር ፈሳሽ ለፆታው ማንነት ትልቁን ሚና ቢጫወትም ባልየው (ወንድ) የፈለገውን ጾታ ሳይሆን አላህ (ሱ.ወ) የወሰነው እንደሚሆን ሊያምነ ይገባል፡፡
ፅንስ በሶሰት ጨለማዎች
—————————-
‹‹በእናታችሁ ሆድ ውስጥ ይፈጥራችኋል በሶሰት ጨለማዎች ውስጥ ስትሆኑ›› (ሱረቱ አል-ዙመር 39 ፡ 6)
ኘሮፌሰር ኪት ሙር እነዚህ በቁርአን የተጠቀሰው ጨለማወችን /ሽፋኖችን/ ሲገልፅ
1. የእናት ሆድ ግድግዳ
2. የማህፀን ግድግዳ
3. በፅንስ ዙሪያ ያለ አምንደ ክርዮኒክ (Amino-chrionic membrane) የሚባል ሽፋን በማለጽ ይገልፃቸዋል፡፡
የፅንስ የመፈጠር ደረጃ
————————
‹‹ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው ከዚያም ጠብታ ዘር ሲሆን በማህፀን ግርግዳ ላይ አሰቀምጠነው ከዚያም የዘር ጠብታውን የረጋ ደም አደረግነው ቀጥሎም የረጋውን ደም ቁራጭ ስጋ አደረግነው ከቁራጭ ስጋውም አጥንቶች አደረግነው አጥንቶቹንም ስጋን አለበስናቸው ከዚያም ሌላ ፍጡር ሆኖ አሳደግነው አሳማሪ (ድንቅ) ፈጣሪ የሆነው አላህ ላቀ›› (ሱረቱ አል-ሙእሚኑን 23፡12-14)
ከላይ በተጠቀሰው አንቀፅ አላህ /ሱ.ወ/. ሰው ከጠብታ እንደተፈጠረና የተጣበቀ ሲሆን በማህፀን ግድግዳ ላይ እንዳሳፈረው (ቀራሪን መኪን) በሚለው የአረብኛ ቃል በመጠቀም ይገልፅልናል፡፡ ማህፀን በጀርባ በኩል በአከርካሪ አጠንት /በጀርባ አጥንት/ እንዲሁም በጀርባ ጡንቻዎት በመታገዝ ይጠበቃል፡፡ ፅንስ ደግሞ ማህፀን ውስጥ በሚገኝ አምንዮቲክ የሚባለውን ፈሳሽ በፅንሱ ዙሪያ በሚይዘው በአንዮቲክ ከረጢት (Amniotic Sac) የተከበበና የተሸፈነ ነው፡፡ ስለሆነም ፅንስ በጣም ጥብቅ በሆነ መከላከያ ስፍራ ነው የተቀመጠው፡፡
ከወንድ የመጣው የዘር ፈሳሽ የማህፀን ግድግደ ላይ ከተለጠፈ በኋላ ወደ የሚጠመጠም ማለትም ወደ ሚዝለገለግ ደም ይቀየራል፡፡ በሌላ በኩል ከዚህ በፊት እንደተገለፀው ይህ የረጋ ደም የአልቅት መሰል ቅርፅ ይኖረዋል፡፡ ሁለቱም አገላለፆች ማለትም በመጀመሪያው የጽንስ ደረጃ በማህፀን ግድግዳ ላይ የተለጠፈው የሚዝለገለግ ደም እና እንዲሁም አልቅት የምትባለውን ጥቃቅን የባክቴሪያ አይነት ቅርስ እንደሚኖረው በሳይንስ ተቀባይነት አግችቷል፡፡ የሚገርመው አልቀትን በቅርጽ ብቻ ሳይሆን የሚመስለው ልክ አልቅት የሰው ልጆች ሰውነት ላይ ተለጥፎ ደም እንደሚመጥ ሁሉ ይህ ፅንስ በማህፀን ግድግዳ ላይ ተለጥፎ የሚያስፈልገውን ምግብ በደም አማካኝነት በእግዴ ልጅ በኩል ያገኛል፡፡
‹‹ዐለቃህ›› የሚለው ሶስተኛ ትርጉም ደግሞ የረጋ ደም ማለት ነው፡፡ በዚህ ‹‹ዐለቃህ›› በሚለው ፅንስ ደረጀ እርግዝና ሶስተኛና አራተኛ ሳምንትን ያሳልፋል፡፡ በዚህ ጊዜ በደም ስሮቹ ላይ በመሆን የረጋ ደም ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት የአልቅትን ቅርፅና የሚዘለግለግ ከመሆኑ በተጨማሪ የረጋ ደም ይመስላል፡፡
በ1677 /እ.ኤ.አ/ ሀምና ሊውንሁክ (Hamm& Leeuwenhoek) የሚባሉት ሳይንቲስቶች የወንድ ዘር ህዋስን (Sperm) ለመጀመሪያ ጊዜ በአጉሊ መነጽር የተመለከቱት ሳይንቲስቶች ናቸው፡፡ እነዚህም ሳይንቲስች የወንድ ዘር ፈሳሽ የማህፀን ግድግዳ ላይ በመለጠፍና በማደግ አዲስ ፍጡር ሆኖ ለሚመጣው ህፃን ሞዴል እንደሆነ አስተማሩ፡፡ ይህ አይነቱ አስተሳሰብ የፐርፎሬሽን (Perforation) ፅንስ ሀሳብ በመባል ይታወቃል፡፡
ከዛ በኃላ ዲግራፍን (De Graf) የመሳሰሉ ሳይንቲስቶች የሴት እንቁላል መጠን ከወንድ የዘር ፈሳሽ የሚበልጥ መሆኑን ሲያረጋግጡ የሚወለደው ልጅ ሞዴል የሴት እንቁላል እንደሆነ ማስተማር ጀመሩ፡፡ ሆኖም በ18ኛው ክፍለ ዘመን ማውፐርቲስ (Maupertuis) የሚባል ተመራማሪ በእንቁላል ወይም በወንድ የዘር ፈሳሽ ላይ ብቻ የተመሰረተ ሳይሆን ከሁለቱም የሚወርሰው ነገር እንዳለ ማስተማር ጀመረ፡፡ በሌላ አነጋገር የሚወለደው ህፃን ከሁለቱም ወላጆቹ ሊወርስ እንደሚችል ገለፀ፡፡
ከላይ በዝርዝር ያየነው “ዐለቃህ” የሚባለው የፅንስ ደረጃ ወደ “ሙድጋህ” ይተላለፋል፡፡ ይህም ማለት (የጥርስ ምልክት ያለው የሚመስል) የታኘከ ስጋ ማለት ሲሆን በአፋችን እንደምንከተው ትንሽ ማስቲካ ማለት ነው፡፡ በሁለቱም መልክ ሲገለፅ ከሳይንስ አንፃር ችግር የለውም፡፡
ኘሮፌሰር ኪት ሙር ከኘላስቲክ የተሰራች የቴምብር ቁራጭ በመውሰድ በመጀመሪያዎቹ የፅንስ ደረጃ ፅንስ ባለው መጠንና ቅርፅ ካደረገ በኃላ አፋ ስር በመክተት በጥርሶቹ መሀል አኘክ አኘክ አደረገው፡፡ ከዚያም ያኘከውን የኘላስቲክ ቴምብር ቁርአን “ሙድጋህ” ብሎ ከጠቀሰው ደረጃ ላይ ፅንስ ባለው የመጀመሪያ ደረጃ የአከርካሪ አጥንት መሰል ነገር ጋር ይመሳሰል፡፡ ይህ የታኘክ ስጋ ወደ አጥንትነት ይለወጣል፡፡ እነዚህ አጥንቶች ደግሞ በስጋና በጡንቻ ይለብሳሉ /ይሸፈናሉ/፡፡ ከዚህም በኃላ አላህ አዲስ ፍጢር አድርጐ ይፈጥረዋል፡፡
ኘሮፌሰር ማርሻል ጆንሰን(Marshal Johnson) አሜሪካ ውስጥ ከሚገኙ ሳይንቲስቶች ዋናው ሲሆን ፊላደልፊያ በሚገኘው የቶማስ ጀፈርሰን ዩኒቪርስቲ ውስጥ በሚገኘው ዳንኤል ጥናትና ምርምር ዳይሬክተርና የሰውነት አካል ቅረፅ (Anatomy) ጥናት ክፍል ዋና ሀላፊ ነው፡፡ በቁርአን ውስጥ ስነ ውልደትን በተመለከተ በተጠቀሰ አንቀጾች ዙሪያ ያለውን ሀሳብ እንዲሰጥ ተጠይቆ ነበር፡፡ ቁርአን ውስጥ የፅንስ ደረጃን በተመለከተ የተቀመጡ እዉነታዎች በአጋጣሚና በግምት እንዳልተጠቀሱ በመግለፅ ሙሀመድ /ሰ.ዐ.ወ/ በጣም ሀይለኛ አጉሊ መነጽር ሳይኖረው አይቀርም ብሎ መልሳ ነበር፡፡ ሆኖም ቁርአን የወረደው ከዛሬ 1400 ዓመት ሰፊት እንደሆነና አጉሊ መነፅር /Micro scope/ የተሰራዉ ከነብዩ መሀመድ /ሰ.ዐ.ወ/ ብዙ ዓመታት በኃላ እንደሆነ ሲነገረው፡፡ ኘሮፌሰር ጆንሰን ፈገግ በማለት እሱ እራሱን እንኳን በነብዩ ሙሀመድ /ሰ.ዐ.ወ/ ጊዜ ቀርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ማይክሮስኮኘ /አጉሊ መነጽር/ ከአስር እጥፍ በላይ ማጉላት የማይችል እንደነበረና የመጀመሪያውን አካባቢ የጽንስ ደረጃ በግልፅ እንደማያሳይ ተቀብሎታል፡፡ በኃላም እንዲህ ብሏል ‹‹በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ግጭት አላገኘሁትም በመሆኑም ሙሀመድ /ሰ.ዐ.ወ”/ ቁርአን ሲያስተም አምላካዊ እገዛ እንደለበት ያስይዛል፡፡›› እንደ ኘሮፌሰር ኪት ሙር አባባል ደግሞ በአሁኑ ሰዓት ዓለም በጠቅላላ የተቀበለው ዘመናዊ ሳይንስ ደረጃ 1 ደረጃ 2 ወዘተ እየተባለ የተከፋፈለው የፅንስ የእድገት ደረጃ በቀላሉ የማይገባና ሊረዲት የማይችል ነው፡፡ ቁርአን የገለፀዉ ፅንስ የሚያፋቸው የአስተዳደግ ደረጃዎች ግልፅ ከመሆናቸውም በላይ በቀላሉ በቅርጽ ለመለየት የሚያስችል ነው፡፡ ከዚህም በላይ የቁርአን አገላለጽ ቅድመ ወሊድ ላይ የተንተራሰ የእድገት ደረጃ ከመግለጹም በላይ ድንቅ የሆነ ለሁሉም የሚገባና ግልጽ ተግባራዊነት ያለው ሳይንሳዊ አገላለጽ ነው፡፡ ተመሳሳይ የሰው ልጅ የፅንስ አስተዳደግን የሚገልጹ አንቀፆችን ማየት ይቻላል፡፡
‹‹(የሰው ልጅ) የሚፈስ የሆነ የሚፈናጠር ጠብታ አልነበረምን ከዚያም የሚዝለገለግ የረጋ ደም ከዚያም(እንዲህ በዚህ መልኩ) አሳምሮ አስተካክሎ ፈጠረው ከሱም ጥንድ ሲሆን ወንድና ሴት አደረገ››(ሱረቱ አል-ቂያማ 75፡37-39)
‹‹በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡ በማንኛውም በፈለገው ቅርጽ በገጣጠመህ›› (ሱረቱ አል-ኢንፊጣር 82፡7-8)
The Qur’an and Modern Science By Dr. Zakir Naik

0 791

ሰው ከጠብታ(አልቅት መሰል ነገር) መፈጠሩ
ከጥቂት ዓመታት በፊት የተወሰኑ አረቦች ባንድ ላይ ሆነው ቁርአን ሰው እንዴት እንደሚወለድ የሚለውን መረጃ ከቁርአን ላይ በመሰብሰብ የሚቀጥለው የቁርአን ትዕዛዝ በመከተል ተንቀሳቀሱ፡፡
‹‹የማታውቁ ከሆነ የእውቀት ባለቤቶች ጠይቁ›› (ሱረቱ አል-ሹዓራእ 26፡43 እና ሱረቱ አል-አንቢያ 21፡7)
በውልደት ዙሪያ የሚገኙን መረጃዎት ከቁርአን ላይ ከሰበሰቡ በኃላ ወደ እንግሊዝኛ በመተርጐም ለኘሮፌሰር ኪትሙር(Keith Moore) አቀረቡለት፡፡ ኘሮፌሰር (ዶ/ር) ኪት ሙር በስነ ውልደት የኘሮፌሰርነት ማዕረግ ሲኖረው በሰውነት ክፍሎች ጥናት / Anatomy/ክፍል ካናዳ በሚገኘው የቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ ዋና ኃላፊ ነው፡፡ ኘሮፌሰር ኪት ሙር በአሁኑ ሰዓት በስነ ውልደት ጥናትና ምርምር አለ የሚባል ምሁር ነው፡፡
በስነ ውልደት ከቁርአን በተውጣጡት መረጃዎት ዙሪያ እሱ ያለውን ሀሳብ እንዲገልጽ ተጠይቆ ነበር፡፡ በዚህ ዙሪያ በእንግሊዝኛ ተተርጉሞ የተሰጠውን የቁርአን አንቀፅ በጥንቃቄ ካጤነውና ከመረመረው በኃላ ኪት ሙር እንዲህ በማለት ይገልፃል ስነ ውልደትን በተመለከተ ቁርአን የሚገልፃቸው መረጃዎት ዘመናዊው ሳይንስ በሰነ ውልደት ጥናትና ምርምር ካገኛቸው ምርምሮች ጋር ፍጽም በሆነ መልኩ ይጣጠማል ምንም አይነት ግጭት የለባቸዉም፡፡ በመቀጠልም ሆኖም የተወሰኑ የቁርአን አንቀጾች የሚገልፁዋቸውን ከሳይንስ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት አስተያየት መስጠት አልፈልግም ትክክል ነው ወይም ስህተት ነው ማለት አልፈልግም ምክንያቱም በነዚህ በተወሰኑ አንቀጾች ዙሪያ ሳይንሳዊ መረጃ አልነበረውም ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ በነዚህ በተወሰኑ የቁርአን አንቀጾች ላይ ዘመናዊ ሳይንስ በጽሑፍ የገለጸው ምንም አይነት መረጃ የለም፡፡ ቁርአን የወረደበት ቋንቁ ማለትም አረብኛ በጣም ያደገና የበለፀገ ነው፡፡ የቃላት ፍቺዎች በጣም ሰፊና ቀላቶች ብዙ ልዩነት አላቸው፡፡ በዚህም ምክንያት በአረብኛ አንዳንድ ቃሎች ወደ ተወሰኑ ወይም ለአንድ ነገር ፍቺ ብቻ የሚያገለግሉ አይደሉም፡፡ ለምሳሌ “ሀሺያ” የሚለው የአረብኛ ቃል ፍቺ ብንመለከት ትርጉሙ “አክብሮታዊ ፍርሀት” ሲሆን ሌሎች ፍርሀቶች ደግሞ የራሳቸው የሆነ የአረብኛ ቃል አላቸው፡፡
ከነዚህ አንቀጾች መሀል አንዱ፡-
“አንብብ ያ በፈጠረህ ጌታህ ስም ሰውን ከረጋ ደም የፈጠረ” (ሱረቱ አል-ዓለቅ 96፡ 1-2)
“አለቅ” የሚለው የአረብኛ ቃል “የረጋ ደም” ከሚለው ትርጉም በተጨማሪ “የሚጣበቅ” “አልቅት መሰል ነገር” የሚሉትም ትርጉም አለው፡፡
በመጀመሪያው የሽል /የተረገዘው/ ደረጃ አልቅትን ይመስል አይመስል ዶ/ር ኪትሙር ምንም አይነት እዉቀት አልንበረውም፡፡ ይህን ለማወቅ በጣም ሀይለኛና ዘመናዊ አጉል መነጽር /Microscope / በመጠቀም ሽል በመጀመሪያ ደረጃ ገና ሲፈጠር ያለበትን ደረጃ በሙከራ /ጥናት/ ክፍል መመልከት ጀመረ፡፡ ከዚያም ያገኘውን መረጃ ከአልቀት ጋር ማወዳዳር ጀመረ እናም በውጤቱ በጣም ተደነቀ በሁለቱ መካከል /በሽሉና በአልቀት/ ከፍተኛ የሆነ መመሳል ተመለከተ /ተገነዘበ/ ልክ እንደዚህ በፊቱ በስነ ውልደት ዙሪያ እስከዛሬ ድረስ የማይታወቀውን ነገር ግን ቁርአን የያዘውን መረጃ በተጨማሪ አረጋገጠ፡፡
በቁርንና በረሱል /ሰ.ዐ.ወ/ ንግግር ውሰጥ /ሀዲስ/ የሚገኙ በስነ ውልደት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ አስራ ስምንት ጥያቄ ተጠይቆ መልስ ሰጥቶ ነበር፡፡ በቁርአንና በሀዲስ ውስጥ የሚገኙት እነዚህ መረጃዎት በቅርቡ ከተገኙ የስነ ውልደት ግኝቶች ጋር ሙሉ በሙሉ ይጣጣማሉ በማለት ኘሮፌሰር ሙር እንዲህ ይላል “እነዚህን ጥያቄዎች ከሰላሳ ዓመት በፊት ብጠየቅ ኖሮ ሳይንሳዊ መረጃዎች ስላልነበሩኝ ግማሹን እንኳ የመመለስ ብቃቱ አይኖረኝም ነበር፡፡”
ዶ/ር ኪት ሙር ከዚህ በፊት ‘’ The Developing Human’’ የሚል መጽሐፍ ጽፎ ነበር፡፡ አዳዲስ እውቀቶችን ከቁርአን አገኘ በኃላ በ1982 /እ.ኤ.አ/ ራሱን ‘’ The Developing Human’’ የሚለውን መጽሐፉን እነዚህን እዉቀቶች በመጨመር ለ3ኛ ጊዜ አሳትሞታል፡፡ ብዙ ጊዜ ሳይንሶዊ መጽሐፎችን ከተመለከታችሁ ሁለት ወይም ሶሰት ሆነው ተረዳድተው ነው የሚያሳትሙት፡፡ ሆኖም ኘሮፌሰር ኪት ሙር በጻፈው ይህ መጽሐፍ በአንድ ግለሰብ የተፃፈ ምርጥ የህክምና መጽሐፍ በመሆን ሽልማት አግኝቶበታል፡፡ ይህ መጽሐፍ በተለያዩ ዋና ዋና በሚባሉ የዓለም ቋንቋዎች ተተርጉሞ በስነውልደት ጥናት የመጀመሪያ ዓመት የህክምና ተማሪዎች ለመማሪያ እየጠተቀሙበት ይገኛል፡፡
በ1981 /እ.ኤ.አ/ በሳውዲ አረቢያ ዲማማ በሚባል ቦታ ለሰባተኛ ጊዜ የተደረገ የህክምና ኮንፈረንስ ላይ ዶ/ር ሙር እንዲህ ይላል “ስለ ሰዎች እድገት የሚናገሩ የቁርአን አንቀፆችንና ዓረፍት ነገሮችን በማብራራቴ በጣም ላቅ ያለና ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል፡፡ እነዚህ ዓረፍት ነገሮች በአምላክ /አላህ/ ወደ ሙሀመድ የመጡ እንደሆነ በጣም ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ እዉቀቶች ሁሉም ማለት ይቻላል ቁርአን ከወረደ ከብዙ ዓመታት በኃላ ነው በሳይንስ የተረጋገጡት፡፡ ይህ ሙሀመድ የአምላክ /አላህ/ መልክተኛ መሆኑን ያረጋግጥልኛል፡፡”
በአሜሪካ በሆሰተን ከተማ በሚገኘው የቤይለር የህክምና ኮሌጅ ውስጥ በፅንስ በማህፀን የትምህርት ክፍል ዋና ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ጆ ሊፍ ሲምኘሰን ሲገልፁ “… እነዚህ የሙሀመድ /ሰ.ዐ.ወ/ አባባሎች /ሀዲስ/ ሙሀመድ በነበረበት ጊዜ ሳይንሶዊ እውቀቶች ኖረው ያገኘው አይደለም፡፡ በሃይማኖቱና /በኢስላም/ በሳይንስ መካከል ምንም አይነት ግጭት አለመኖር ብቻ ሳይሆን ሀይማኖቱ /ኢስላም/ ወደ ሳይንስ ይመራል … ቁርአን መሆናቸው የተረጋገጡ በቁርአን ውስጥ የሚገኙ አንቀጾች ቁርአን ከአምላክ የወረደ ቅዱስ መጸሐፍ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡”
ሰው የተፈጠረበት ጠብታ-
—————————–
“ሰው ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት እሱ ከሚፈናጠር ጠብታ ውሃ ተፈጠረ፡፡ ከጀርባ አጥንትና ከጐድን አጥንት ከእርግብግቢቶች መካከል ከሚወጣ ከሆነ” (ሱረቱ አል-ጣሪቅ 86፡5 -7)
በሽል መፈጠር ጊዜ የወንድና የሴት መራቢያ አካሎች ማለትም በወንዱ ብልት ስር የሚገኙና ፍሬዎች የወንድና ዘር /Sperm/ የሚያመርተው፣ /Ovary/ የሚባለው የሴትን እንቁላል የሚያመርተው ሁለቱም እድገታቸዉ የሚጀምረው በኩላሊት አካባቢ በ11ኛውና በ12ኛው የጐድን አጥንትና በከርካሪ አጥንት መሀል ነው፡፡ ከዚያም ሁለቱም ከዚህ አካባቢ ይወርዳሉ፡፡ የሴት እንቁላል አምራች /Ovary/ እስከ የወገብ አጥንት ይወርድሃ ይቆማል፡፡ የወንድ ዘር ማምረቻው /Testicle/ ግን ብልት ስር ባለው ፊኛ ስር ይወርዳል፡፡ ሌላው ቀርቶ ለአቅመ አዳምና ለአቅመ ሄዋን ሲደርሱ እነዚህ የመራቢያ አካሎች የነርቭ መልዕክትና ደም በአከርካሪና በጐድን አጥንት መሀከል ከሚገኘውና ሆድ አካባቢ ከሚገኘው ትልቁ የደም ቧንቧ ይቀበላሉ፡፡
ሰው ከጥቂት ጠብታ ተፈጠረ (በጣም ትንሽ ከሆነ ጠብታ)
——————————————————
በተከበረው ቁርአን “ኑጥፋህ” ማለት በጣም ጥቂት በሆነ ጠብታ ለምሳሌ እርጥብ በዶ ሰኒን በአፉ ሲደፋ ሊመጣ ከሚችል ጥቂት ጠብታ የሰውን ልድ ፈጠርነው ሲል ከአስር ጊዜ ያላነሰ ቦታ ገልጿል፡፡ ይህ በተለያዩ የቁርአን አንቀጾች 25፡2 ና 23፡12 ጨምሮ ገልጾበታል፡፡
አንድ የሴት እንቁላልን ለማስፈልፈል /እንዲፀንስ ለማድረግ/ ወይም ለማስፀነስ በአማካኝ ከሶስት ሚሊዮን የወነድ ዘሮች /Sperm/ አንዷ በቂ ነች፡፡ ይህ ማለት 1/3 ወይም 0.0003 ወይም ከ3000000 የወንድ ዘር አንዷ ብቻ ታስፀንሳለች፡፡
ሰዎች ከሚያስጠላው ግን ምርጥ
———————————–
“ከዚያም ዘሮቹን ከተንጣለለ ከደከማ ውሃ ያደረገ ነው” (ሱረቱ አል-ሰጅዳ 32፡8)
ሱላላህ ማለት ካሉ ሁሉ ምርጥ /ከተንጣለለ/ ከሆነው ማለት ነው፡፡ በዚህ አንቀጽ አንድ ነገር እናውቃለን፡፡ የሴቷን እንቁላል ለማፀነስ አንድ የወንድ ዘር /sperm/ በቂ ነው፡፡ ከብዙ ሚሉዬን ከሚቆጠር የወንድ ዘሮች ማለት ነው፡፡ ከነዛ ሁሉ ብዙ ሚሊዬን አንዷ ዘር /sperm/ ሱላላህ ትባላለች፡፡ በሌላ በኩል ከፈሳሽ ውስጥ ረጋ ብሎ ተነጥሎ መውጣት ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ ፈሳሽ ሲባል ለሁለቱም የወንዱም የሴቱም የዘር ፈሳሽ ይመለከታል፡፡ እንቁላልም ይሁን የወንድ ዘር /sperm/ ረጋ ብለው ነው የሚወጡት፡፡
ሰው ከተቀላቀለ ጠብታ ተፈጠረ
———————————-
እኛ ሰውን /በህግ ግዳጅ/ የምንሞክረው ስንኾን ቅልቅሎች ከሆኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው ሰሚ ተመልካችም አደረግነው፡፡(ሱረቱ አል-ኢንሳን 76፡2)
ኑጥፈተን አምሻድ ማለት የተቀላቀለ የፈሳሽ ጠብታ ሲሆን አንዳንድ የቁርአን የትርጉም ሊቆች የተቀላቀለ የፈሳሸ ጠብታ የሚለውን ሲተረጉሙ ከወንድ የዘር ፈሳሽና ከሴቷ እንቁላል ፈሳሽ በማለት ይተረጉማሉ፡፡ የሁለቱ ፆታዎች ፈሳሽ ከተቀላቀለ በኃላ ራሱ የሚፈጠረው ህዋስ /Cell/ በፈሳሽ መልክ ይቆያል፡፡ የተቀላቀለ የፈሳሽ ጠብታ የሚለው ለወንድ የዘር ፈሳሽ ብቻም ሊያገለግል ይችላል፡፡ ምክንያቱም የወንድ የዘር ፈሳሽ ሰውነት ውስጥ ከሚመነጨው የተለያዩ ፈሳሾች የተፈጠረ ስለሆነ፡፡
የፅንስ ወንድ ወይም ሴት መሆን
——————————-
ለሽል ፆታ ዋናውን ሚና የሚጫወተው የወንድ የዘር ፈሳሽ እንጂ የሴት እንቁላል አይደለም፡፡ የሚወለደው ህፃን ፆታ ማለትም ሴት ይሁን ወንድ የሚመሰረተው ባለ ሃያ ሶስት ጥንድ /Chromosomes/ ከሆኑ የእናትና ባህሪ ከሚይዘው እንቁላልና ባለሃያ ሶስት ጥንድ /Chromosomes/ የአባትን ባህሪ ከሚይዘው የወንድ ዘር ሆኖ የሴቷ xx በሚል ሲገልፅ የወንዱ በ xy ይገለፃል፡፡
በመጀመሪያው ደረጃ ፆታን የሚለየው ልክ እንደተፀነስ ሲሆን የሴቷን እንቁላል ከሚያስፀንሰው በወንዴው የዘር ፈሳሽ ውስጥ ባለው ክሮሞዛም /Chromosomes/ በሚባል Chemical ይወሰናል፡፡ ከላይ እንደተገለፀው የወንዴው በ xy ሲሆን የሴቷ ከ xx ተብሎ ሲገለጽ በሚችል ነው ዘር የተሰራው፡፡ የወንዴው ዘርና የሴቷ ዘር ሲገናኙ በመጀመሪያ ደረጃ ህዋሶቹ ይለያያዩ የወንዴዉ የነበረው xy የነበረው x እና y ይሆናል የሴት ደግሞ xx የነበረው x ና x ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት ፅንስ የሚፈጠረው x ከሚባለው የወንዴ ዘር ከሆነ ከሴቷ x ብቻ ስለሚመጣ xx ይሆናል ይህ ማለት ሴት ነው ማለት ነው ሆኖም ከወንዴው y ከመጣ xy ይሆንና ወንድ ይሆናል ማለት ነው፡፡
‹‹ወንድና ሴትን በጥንድ ፈጠረ ከሚፈናጠር ከሆነው የፈሳሽ ጠብታ›› ሱረቱ አል-ነጅም 53፡ 45 – 46)
ከዚህ በፊት እንዳየነው /ኑጥፋህ/ ማለት ጠብታ ሲሆን /ቱምና/ የሚለው የአረብኛ ቃል ትርጉሙ የሚፈናጠር፣ የሚረጭ፣ የሚለጠፍ ይሆናል፡፡ የሚፈናጠርዋ የሚራጭ፣ የሚለጠፍ ደግሞ የወንድ ዘር ነው፡፡ ስለዚህ ከሴቷ እንቁላል ለየት አድርጐ የሰው ልጅ ወንድም ይሁን ሴቱን ከወንድ ዘር እንደተፈጠረ ይገልፃል፡፡ ይህ ከላይ እንደገለፅኩት ለፆታ ወሰኙ የወንድ ዘር እንደሆነ ያስገነዝበናል፡፡
ቁርአን በሌላ አንቀፅም እንዲህ ይላል፡-
‹‹(የሰው ልጅ) የሚረጭ፣ የሚፈናጠር ጠብታ አልነበረምን ከዚያ የረጋ ደም አልሆነም እናም (አላህ) በሚያምር ሁኔታ (እንዲህ በዚህ መልኩ) ፈጠረው ከሱም ጥንድ ሲሆኑ ወንድና ሴትን አደረገ›› (ሱረቱ አል-ቂያማ 75፡37 – 39)
እዚህም ጋር ጥቂቷን ጠብታ በመግለፅ ለፅንስ ፆታ ወሳኙን ቦታ የሚይዘው የወንድ የዘር ፈሳሽ እንደሆነ ይገልፃል፡፡
በተለምዶ በህንደ አገር ውስጥ አማት የልጅ ልጇ ወንድ እንዲሆንላት ጥልቅ የሆነ ፍለጐት አላት እናም የተወለደው ልጅ የምትፈለገውን አይነት ፆታ ከሌለው ምክንያቷ ምራቷ /የልጇ ሚስት/ ነች በማለት ትወቅሳለች፡፡ የሚወለደው ፆታን በተመለከተ ወሳኙ የወንድ የዘር ፈሳሽ እንጂ የሴት እንቁላል አለመሆኑን ቢያውቁና መውቀስ አለብን ብለው የሚያምኑ ከሆነ ምራታቸውን ሳይሆን እራሱ ልጃቸውን ተጠያቂ ማድረግ ነበረባቸው ምክንያቱም በቁርአንም ይሁን በሳይንስ ለሚወለደው ህፃን ፆታ ወሳኙ የወንድ የዘር ፈሳሽ እንጂ የሴቷ አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ አንድ ሙስሉም የወንድ የዘር ፈሳሽ ለፆታው ማንነት ትልቁን ሚና ቢጫወትም ባልየው (ወንድ) የፈለገውን ጾታ ሳይሆን አላህ (ሱ.ወ) የወሰነው እንደሚሆን ሊያምነ ይገባል፡፡
ፅንስ በሶሰት ጨለማዎች
—————————-
‹‹በእናታችሁ ሆድ ውስጥ ይፈጥራችኋል በሶሰት ጨለማዎች ውስጥ ስትሆኑ›› (ሱረቱ አል-ዙመር 39 ፡ 6)
ኘሮፌሰር ኪት ሙር እነዚህ በቁርአን የተጠቀሰው ጨለማወችን /ሽፋኖችን/ ሲገልፅ
1. የእናት ሆድ ግድግዳ
2. የማህፀን ግድግዳ
3. በፅንስ ዙሪያ ያለ አምንደ ክርዮኒክ (Amino-chrionic membrane) የሚባል ሽፋን በማለጽ ይገልፃቸዋል፡፡
የፅንስ የመፈጠር ደረጃ
————————
‹‹ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው ከዚያም ጠብታ ዘር ሲሆን በማህፀን ግርግዳ ላይ አሰቀምጠነው ከዚያም የዘር ጠብታውን የረጋ ደም አደረግነው ቀጥሎም የረጋውን ደም ቁራጭ ስጋ አደረግነው ከቁራጭ ስጋውም አጥንቶች አደረግነው አጥንቶቹንም ስጋን አለበስናቸው ከዚያም ሌላ ፍጡር ሆኖ አሳደግነው አሳማሪ (ድንቅ) ፈጣሪ የሆነው አላህ ላቀ›› (ሱረቱ አል-ሙእሚኑን 23፡12-14)
ከላይ በተጠቀሰው አንቀፅ አላህ /ሱ.ወ/. ሰው ከጠብታ እንደተፈጠረና የተጣበቀ ሲሆን በማህፀን ግድግዳ ላይ እንዳሳፈረው (ቀራሪን መኪን) በሚለው የአረብኛ ቃል በመጠቀም ይገልፅልናል፡፡ ማህፀን በጀርባ በኩል በአከርካሪ አጠንት /በጀርባ አጥንት/ እንዲሁም በጀርባ ጡንቻዎት በመታገዝ ይጠበቃል፡፡ ፅንስ ደግሞ ማህፀን ውስጥ በሚገኝ አምንዮቲክ የሚባለውን ፈሳሽ በፅንሱ ዙሪያ በሚይዘው በአንዮቲክ ከረጢት (Amniotic Sac) የተከበበና የተሸፈነ ነው፡፡ ስለሆነም ፅንስ በጣም ጥብቅ በሆነ መከላከያ ስፍራ ነው የተቀመጠው፡፡
ከወንድ የመጣው የዘር ፈሳሽ የማህፀን ግድግደ ላይ ከተለጠፈ በኋላ ወደ የሚጠመጠም ማለትም ወደ ሚዝለገለግ ደም ይቀየራል፡፡ በሌላ በኩል ከዚህ በፊት እንደተገለፀው ይህ የረጋ ደም የአልቅት መሰል ቅርፅ ይኖረዋል፡፡ ሁለቱም አገላለፆች ማለትም በመጀመሪያው የጽንስ ደረጃ በማህፀን ግድግዳ ላይ የተለጠፈው የሚዝለገለግ ደም እና እንዲሁም አልቅት የምትባለውን ጥቃቅን የባክቴሪያ አይነት ቅርስ እንደሚኖረው በሳይንስ ተቀባይነት አግችቷል፡፡ የሚገርመው አልቀትን በቅርጽ ብቻ ሳይሆን የሚመስለው ልክ አልቅት የሰው ልጆች ሰውነት ላይ ተለጥፎ ደም እንደሚመጥ ሁሉ ይህ ፅንስ በማህፀን ግድግዳ ላይ ተለጥፎ የሚያስፈልገውን ምግብ በደም አማካኝነት በእግዴ ልጅ በኩል ያገኛል፡፡
‹‹ዐለቃህ›› የሚለው ሶስተኛ ትርጉም ደግሞ የረጋ ደም ማለት ነው፡፡ በዚህ ‹‹ዐለቃህ›› በሚለው ፅንስ ደረጀ እርግዝና ሶስተኛና አራተኛ ሳምንትን ያሳልፋል፡፡ በዚህ ጊዜ በደም ስሮቹ ላይ በመሆን የረጋ ደም ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት የአልቅትን ቅርፅና የሚዘለግለግ ከመሆኑ በተጨማሪ የረጋ ደም ይመስላል፡፡
በ1677 /እ.ኤ.አ/ ሀምና ሊውንሁክ (Hamm& Leeuwenhoek) የሚባሉት ሳይንቲስቶች የወንድ ዘር ህዋስን (Sperm) ለመጀመሪያ ጊዜ በአጉሊ መነጽር የተመለከቱት ሳይንቲስቶች ናቸው፡፡ እነዚህም ሳይንቲስች የወንድ ዘር ፈሳሽ የማህፀን ግድግዳ ላይ በመለጠፍና በማደግ አዲስ ፍጡር ሆኖ ለሚመጣው ህፃን ሞዴል እንደሆነ አስተማሩ፡፡ ይህ አይነቱ አስተሳሰብ የፐርፎሬሽን (Perforation) ፅንስ ሀሳብ በመባል ይታወቃል፡፡
ከዛ በኃላ ዲግራፍን (De Graf) የመሳሰሉ ሳይንቲስቶች የሴት እንቁላል መጠን ከወንድ የዘር ፈሳሽ የሚበልጥ መሆኑን ሲያረጋግጡ የሚወለደው ልጅ ሞዴል የሴት እንቁላል እንደሆነ ማስተማር ጀመሩ፡፡ ሆኖም በ18ኛው ክፍለ ዘመን ማውፐርቲስ (Maupertuis) የሚባል ተመራማሪ በእንቁላል ወይም በወንድ የዘር ፈሳሽ ላይ ብቻ የተመሰረተ ሳይሆን ከሁለቱም የሚወርሰው ነገር እንዳለ ማስተማር ጀመረ፡፡ በሌላ አነጋገር የሚወለደው ህፃን ከሁለቱም ወላጆቹ ሊወርስ እንደሚችል ገለፀ፡፡
ከላይ በዝርዝር ያየነው “ዐለቃህ” የሚባለው የፅንስ ደረጃ ወደ “ሙድጋህ” ይተላለፋል፡፡ ይህም ማለት (የጥርስ ምልክት ያለው የሚመስል) የታኘከ ስጋ ማለት ሲሆን በአፋችን እንደምንከተው ትንሽ ማስቲካ ማለት ነው፡፡ በሁለቱም መልክ ሲገለፅ ከሳይንስ አንፃር ችግር የለውም፡፡
ኘሮፌሰር ኪት ሙር ከኘላስቲክ የተሰራች የቴምብር ቁራጭ በመውሰድ በመጀመሪያዎቹ የፅንስ ደረጃ ፅንስ ባለው መጠንና ቅርፅ ካደረገ በኃላ አፋ ስር በመክተት በጥርሶቹ መሀል አኘክ አኘክ አደረገው፡፡ ከዚያም ያኘከውን የኘላስቲክ ቴምብር ቁርአን “ሙድጋህ” ብሎ ከጠቀሰው ደረጃ ላይ ፅንስ ባለው የመጀመሪያ ደረጃ የአከርካሪ አጥንት መሰል ነገር ጋር ይመሳሰል፡፡ ይህ የታኘክ ስጋ ወደ አጥንትነት ይለወጣል፡፡ እነዚህ አጥንቶች ደግሞ በስጋና በጡንቻ ይለብሳሉ /ይሸፈናሉ/፡፡ ከዚህም በኃላ አላህ አዲስ ፍጢር አድርጐ ይፈጥረዋል፡፡
ኘሮፌሰር ማርሻል ጆንሰን(Marshal Johnson) አሜሪካ ውስጥ ከሚገኙ ሳይንቲስቶች ዋናው ሲሆን ፊላደልፊያ በሚገኘው የቶማስ ጀፈርሰን ዩኒቪርስቲ ውስጥ በሚገኘው ዳንኤል ጥናትና ምርምር ዳይሬክተርና የሰውነት አካል ቅረፅ (Anatomy) ጥናት ክፍል ዋና ሀላፊ ነው፡፡ በቁርአን ውስጥ ስነ ውልደትን በተመለከተ በተጠቀሰ አንቀጾች ዙሪያ ያለውን ሀሳብ እንዲሰጥ ተጠይቆ ነበር፡፡ ቁርአን ውስጥ የፅንስ ደረጃን በተመለከተ የተቀመጡ እዉነታዎች በአጋጣሚና በግምት እንዳልተጠቀሱ በመግለፅ ሙሀመድ /ሰ.ዐ.ወ/ በጣም ሀይለኛ አጉሊ መነጽር ሳይኖረው አይቀርም ብሎ መልሳ ነበር፡፡ ሆኖም ቁርአን የወረደው ከዛሬ 1400 ዓመት ሰፊት እንደሆነና አጉሊ መነፅር /Micro scope/ የተሰራዉ ከነብዩ መሀመድ /ሰ.ዐ.ወ/ ብዙ ዓመታት በኃላ እንደሆነ ሲነገረው፡፡ ኘሮፌሰር ጆንሰን ፈገግ በማለት እሱ እራሱን እንኳን በነብዩ ሙሀመድ /ሰ.ዐ.ወ/ ጊዜ ቀርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ማይክሮስኮኘ /አጉሊ መነጽር/ ከአስር እጥፍ በላይ ማጉላት የማይችል እንደነበረና የመጀመሪያውን አካባቢ የጽንስ ደረጃ በግልፅ እንደማያሳይ ተቀብሎታል፡፡ በኃላም እንዲህ ብሏል ‹‹በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ግጭት አላገኘሁትም በመሆኑም ሙሀመድ /ሰ.ዐ.ወ”/ ቁርአን ሲያስተም አምላካዊ እገዛ እንደለበት ያስይዛል፡፡›› እንደ ኘሮፌሰር ኪት ሙር አባባል ደግሞ በአሁኑ ሰዓት ዓለም በጠቅላላ የተቀበለው ዘመናዊ ሳይንስ ደረጃ 1 ደረጃ 2 ወዘተ እየተባለ የተከፋፈለው የፅንስ የእድገት ደረጃ በቀላሉ የማይገባና ሊረዲት የማይችል ነው፡፡ ቁርአን የገለፀዉ ፅንስ የሚያፋቸው የአስተዳደግ ደረጃዎች ግልፅ ከመሆናቸውም በላይ በቀላሉ በቅርጽ ለመለየት የሚያስችል ነው፡፡ ከዚህም በላይ የቁርአን አገላለጽ ቅድመ ወሊድ ላይ የተንተራሰ የእድገት ደረጃ ከመግለጹም በላይ ድንቅ የሆነ ለሁሉም የሚገባና ግልጽ ተግባራዊነት ያለው ሳይንሳዊ አገላለጽ ነው፡፡ ተመሳሳይ የሰው ልጅ የፅንስ አስተዳደግን የሚገልጹ አንቀፆችን ማየት ይቻላል፡፡
‹‹(የሰው ልጅ) የሚፈስ የሆነ የሚፈናጠር ጠብታ አልነበረምን ከዚያም የሚዝለገለግ የረጋ ደም ከዚያም(እንዲህ በዚህ መልኩ) አሳምሮ አስተካክሎ ፈጠረው ከሱም ጥንድ ሲሆን ወንድና ሴት አደረገ››(ሱረቱ አል-ቂያማ 75፡37-39)
‹‹በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡ በማንኛውም በፈለገው ቅርጽ በገጣጠመህ›› (ሱረቱ አል-ኢንፊጣር 82፡7-8)
ስነ – ውልደት ክፍል 2 በሚቀጥለው ሳምንት ይዘን እንቀርባለን ኢንሻ አላህ
Reference Book:- The Qur’an and Modern Science By Dr. Zakir Naik

ተርጉመው ላቀረቡልን አላህ ምንዳቸውን ይክፈላቸው